La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 17:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ሲኦል ይወርዳልን? አብረን ወደ አፍር ውስጥ እንገባ የለምን?”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ሞት ደጅ ይወርዳልን? ዐብረንስ ወደ ትቢያ እንሄዳለንን?”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ ወደ ሲኦል ስወርድ ተስፋ አብሮኝ ይወርዳልን? አብረንስ ወደ መቃብር እንወርዳለንን?”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእ​ኔስ ጋር ወደ መቃ​ብር ትወ​ር​ዳ​ለ​ችን? አብ​ረ​ንስ በመ​ሬት ውስጥ እን​ቀ​በ​ራ​ለ​ንን?”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብረን በመሬት ውስጥ ስናርፍ፥ ወደ ሲኦል ይወርዳል።

Ver Capítulo



ኢዮብ 17:16
14 Referencias Cruzadas  

ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ፥ እንዲህም አለ፦


አጥንቶቹ በወጣት ኃይል ተሞልተው ነበር፥ ነገር ግን አሁን ያ የወጣትነት ኃይሉ ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።”


የሸለቆው ጓል ይጣፍጥለታል፥ በኋላውም ሰው ሁሉ ይከተለዋል፥ በፊቱም ቍጥር የሌለው ጉባኤ አለ።


ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ይቸኩላሉ፥ ያለ ተስፋም ያልቃሉ።”


ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንዲሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግመኛ አይወጣም።


አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥ ፊትህን ከኔ አትሰውር፥ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።


ውኆች እስከ ነፍሴ ድረስ ከበቡኝ፤ ጥልቁ ባሕር ከበበኝ፥ የባሕሩ ሣር በራሴ ተጠመጠመ።


በእርግጥም፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ የሞት ፍርድ እንደተላለፈብን በውስጣችን ተሰምቶን ነበር።