ኢዮብ 15:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መከራና ጭንቀት ያስፈራሩታል፥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ ያሸንፉታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጭንቀትና ሐዘን ያስፈራሩታል፤ ለማጥቃት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥም ያይሉበታል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጨለማው ጊዜ አስፈራራው፤ አንድ ንጉሥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ዐይነት ሐዘንና ጭንቀት ይበረቱበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከራና ጭንቀት ይመጡበታል፤ በፊት እንደ ተሰለፈ መኰንን ይወድቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከራና ጭንቀት ያስፈራሩታል፥ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ ያሸንፉታል። |
ስለ ይሁዳም ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ በል፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ “የባቢሎን ንጉሥ በእርግጥ ይመጣል ይህችንም አገር ያፈርሳታል፥ ከሰውና ከእንስሳም ባዶ ያደርጋታል በማለት ለምን ጻፍህበት?” ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል።