143 መከራና ችግር አገኙኝ፥ ትእዛዛትህ ግን ተድላዬ ናቸው።
143 መከራና ሥቃይ ደርሶብኛል፤ ነገር ግን ትእዛዝህ ደስታዬ ነው።
143 ብዙ ችግርና ጭንቀት ደርሶብኛል፤ ትእዛዞችህ ግን ደስታን ይሰጡኛል።
ከተናገራቸው ትእዛዛት አልኮበለልኩም፥ የአፉን ቃል በልቤ ደብቄአለሁ።
የሞት ገመዶች ወጠሩኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፥ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።
እጅግ ተቸገርሁ፥ አቤቱ፥ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
በድንጋጌዎችህ ደስ ይለኛል፥ ቃልህንም አልረሳም።
እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።
ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር።
የዕርገት መዝሙር። አቤቱ፥ አንተን ከጥልቅ ጠራሁህ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ ማድረግ፥ ሥራውንም መፈጸም ነው።