ኢዮብ 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥ እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ዕድሜ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፤ የወራቱንም ብዛት ወስነህ አስቀምጠሃል፤ ሊያልፈው የማይችለውንም ገደብ አኖርህለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፤ የሚኖርባቸውም ወራት በአንተ ዘንድ የተቈጠሩ ናቸው፤ አንተም ከወሰንክለት የዕድሜ ገደብ የሚያልፍ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤ ወሮቹም በአንተ ዘንድ የተቈጠሩ ናቸው፤ ዘመኑንም ወስነህ ትሰጠዋለህ፤ እርሱም ከዚያ አያልፍም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥ እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት። |
መንፈስን ለማገድ በመንፈስ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፥ በሞቱም ቀን ላይ ሥልጣን የለውም፥ በጦርነትም ውስጥ መሰናበቻ የለም፥ ክፋትም ሠሪውን አያድነውም።
ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።
“በፊላደልፊያም ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ ‘ቅዱስና እውነተኛ የሆነው፥ የዳዊትም መክፈቻ ያለው፥ ሲከፍትም፥ ማንም የማይዘጋው፤ ሲዘጋም ማንም የማይከፍተው፤ እርሱ እንዲህ ይላል’፦