Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 104:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ፥ ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ፊትህን ስትሰውር፣ በድንጋጤ ይሞላሉ፤ እስትንፋሳቸውንም ስትወስድባቸው ይሞታሉ፤ ወደ ዐፈራቸውም ይመለሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 አንተ ስትለያቸው ሁሉም ይደነግጣሉ፤ እስትንፋሳቸውን ስትወስድባቸውም ይሞታሉ፤ ወደ ተገኙበትም ዐፈር ይመለሳሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ውኃ​ቸ​ውን ደም አደ​ረገ፥ ዓሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ገደለ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 104:29
12 Referencias Cruzadas  

አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።


ነፍሱ ትወጣለች ወደ መሬቱም ይመለሳል፥ ያንጊዜ እቅዶቹ በሙሉ ይጠፋሉ።


እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና፥ አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።


ሰውን ወደ አፈር ትመልሳለህ፥ “የሰው ልጆች ሆይ”፥ ተመለሱ ትላለህ፥


እኔም በደስታዬ፦ ለዘለዓለም አልታወክም አልሁ።


“ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በግንባርህ ላብ እንጀራን ትበላለህ፥ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።”


ከጭቃ እንደሠራኸኝ አስታውስ፥ ወደ ትቢያም ትመልሰኛለህን?


በዚያች ቀን እቀጣቸዋለሁ፤ እተዋቸዋለሁም፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያችም ቀን፥ ‘ይህ ጥፋት የደረሰብን፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን?’ ይላሉ።


ሕዝብንም ሆነ ሰውን በተመለከተ፥ ዝም ቢል የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?


ፊትህን ለምን ትሰውራለህ? እንደ ጠላትህም የቈጠርኸኝ ለምንድነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios