Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 12:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ ናት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የፍጥረት ሁሉ ሕይወት፣ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናትና፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሕይወት ያለው ፍጥረት ሁሉና የእያንዳንዱም ሰው ነፍስ በእግዚአብሔር ሥልጣን ሥር ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የሕ​ያ​ዋን ሁሉ ነፍስ፥ የሰ​ውም ሁሉ መን​ፈስ በእጁ ናትና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የሕያዋን ሁሉ ነፍስ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናት።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 12:10
17 Referencias Cruzadas  

ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ ‘እኛ ደግሞ ዘመዶቹ ነንና፤’ ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንንቀሳቀሳለን፤ እንኖርማለን።


የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ።


እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና፥ አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።


እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው በመስገድ እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ! አንተ የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን?”


እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥


ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ፥ ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ።


ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።


ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።


እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል።


እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በወሰደ ጊዜ፥ አምላክን የካደ ሰው ተስፋው ምንድነው?


ጻድቃንና ጠቢባን፥ ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፥ ፍቅርም ሆነ ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም፤ ሁሉም በፊታቸው ነው።


ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፥ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፥ በእርሷ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፥ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦


መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም፥ የምድርንም ፊት ታድሳለህ።


መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘለዓለም አልጣላም፥ ሁልጊዜም አልቈጣም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios