ኢዮብ 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰውም እንዲሁ ተኝቶ አይነሣም፥ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥ ከእንቅልፉም አይነሣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም ሰው ይተኛል፤ ቀናም አይልም፤ ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ ከእንቅልፉም አይነሣም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውም እንዲሁ ከሞተ በኋላ አይመለስም፤ ሰማይ እስከሚያልፍ ድረስ አይነቃም፤ ከእንቅልፉም አይነሣም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ከተኛ በኋላ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፤ ከእንቅልፉም አይነሣም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም ተኝቶ አይነሣም፥ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥ ከእንቅልፉም አይነሣም። |
ሰው ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖር በሁሉም ደስ ይበለው፥ ሆኖም የጨለማውን ዘመን ያስብ፥ ብዙ ቀን ይሆናልና። የሚመጣው ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።
ከፍ ያለውን ደግሞ ሲፈሩ፥ ድንጋጤም በመንገድ ላይ ሲሆን፥ ለውዝም ሲያብብ፥ አንበጣም እንደ ሸክም ሲከብድ፥ ፈቃድም ሲጠፋ፥ ሰው ወደ ዘለዓለም ቤት ሲሄድ፥ አልቃሾችም በአደባባይ ሲዞሩ፥
ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ፥ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያትን እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፥ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፥ የሚኖሩባትም እንዲሁ ይሞታሉ፤ ማዳኔ ግን ለዘለዓለም ይሆናል፥ ጽድቄም አይፈርስም።
ነገር ግን አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር በዚሁ ቃል፥ እግዚአብሔርን የማያመልኩት ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀው ይቆያሉ።