Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፥ አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ይህን ጊዜ በሰላም በተኛሁ፣ አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አሁን በሰላም በተጋደምኩ፥ አንቀላፍቼም ዕረፍት ባገኘሁ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አሁ​ንም ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፤ አን​ቀ​ላ​ፍ​ቼም ባረ​ፍሁ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፥ አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 3:13
22 Referencias Cruzadas  

አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


አንድ ሰው በሰላም ተረጋግቶ ሲቀመጥ ከነሙሉ ኃይሉ ሳለ ይሞታል።


ዕድሜያቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ፥ በሰላምም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ።”


እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዐይኖቼም ይመለከቱታል፥ ከእኔም ሌላ አይደለም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።


ተስፋ ባደርግ ሲኦል ቤቴ ናት፥ ምንጣፌንም በጨለማ ዘርግቻለሁ።


እንደ ጨለማም ወደ ጨለመች፥ ሥርዓትም ወደሌለባት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ፥ ልቀቀኝም።”


ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”


ጉልበቶች ስለምን ተቀበሉኝ? ጡትስ ስለምን ጠባሁ?


ወደማልመለስበት ስፍራ ሳልሄድ፥ ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ ምድር፥


ለዘለዓለም ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፥ ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ።


ጥቂት ዓመታት ካለፉ በኋላ እኔ ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።”


እኔን ግን የሚቤዥኝ ሕያው እንደሆነ፥ በመጨረሻም ዘመን በምድር ላይ እንደሚቆም፥


በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይተኛሉ፥ ትልም ይከድናቸዋል።


ድርቅና ሙቀት የበረዶውን ውኃ ያጠፋሉ፥ እንዲሁ ሲኦል በደለኞችን ታጠፋለች።


ማኅፀን ትረሳዋለች፥ ትልም በደስታ ይጠባዋል፥ ዳግመኛም የሚያስታውሰው የለም፥ ክፋትም እንደ ዛፍ ይሰበራል።”


ሙታን ከውኆች በታች፥ በውኆችም ውስጥ ከሚኖሩ በታች ይንቀጠቀጣሉ።


ሲኦል በፊቱ ራቁትዋን ናት፥ ለጥፋትም መጋረጃ የለውም።


ክፋትን የሚሠሩ የሚደበቁበት ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም።


ከወደቁ ኃያላን ካልተገረዙ የጦር መሣሪያቸውን ይዘው፥ ሰይፋቸውንም ከራስጌያቸው በታች አድርግው ወደ ሲኦል ከወረዱ ጋር አልተኙም፥ በሕያዋንም ምድር ያሸብሩ ስለ ነበር ኃጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ነበር


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios