ኢዮብ 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታዲያ ክፋቴን የምትከታተለው፥ ኃጢአቴንም የምትመረምረው ለምንድን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ ኀጢአቴንም የምትከታተለው ለምንድን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔን በደል የምትመለከት፥ ኃጢአቴንም የምትከታተለው፥ ለምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፋቴን ትፈላለግ ዘንድ፥ ኀጢኣቴንም ትመረምር ዘንድ፥ |
በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ በአተላቸውም ላይ የሚረጉትን፥ በልባቸውም፦ “ጌታ መልካምም ክፉም አያደርግም” የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።
ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።