Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የእኔን በደል የምትመለከት፥ ኃጢአቴንም የምትከታተለው፥ ለምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ታዲያ፣ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ ኀጢአቴንም የምትከታተለው ለምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ታዲያ ክፋቴን የምትከታተለው፥ ኃጢአቴንም የምትመረምረው ለምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ክፋ​ቴን ትፈ​ላ​ለግ ዘንድ፥ ኀጢ​ኣ​ቴ​ንም ትመ​ረ​ምር ዘንድ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 10:6
13 Referencias Cruzadas  

ለመሆኑ የሠራሁት በደልና ኃጢአት ምን ያኽል ነው? እስቲ መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ።


እነሆ አሁን እርምጃዬን ሁሉ ትከታተላለህ፤ ሆኖም ኃጢአቴን አታስብብኝም።


“እኔ የማዝነው በሰብአዊ ፍጡር ላይ ነውን? ታዲያ፥ ትዕግሥቴ ቢያልቅ ምን ያስገርማል?


ታዲያ፥ ‘እግዚአብሔር የሰውን አቤቱታ አይሰማም’ በማለት ለምን በእግዚአብሔር ላይ ታማርራለህ?


አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን?


የኃጢአተኞችንና የክፉ ሰዎችን ኀይል አድክም፤ ከእንግዲህ ወዲያ ክፋትን እንዳያደርጉ በክፉ ሥራቸው ሁሉ ቅጣቸው።


አንተ የተሰወረውን ሐሳባችንን ስለምታውቅ በደላችንን ገልጠህ ባየህብን ነበር።


ልብሶችሽ በንጹሖችና በድኾች ደም ተበክለዋል። “ነገር ግን ይህን ሁሉ አድርገሽ፥ ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤ በእርግጥ እግዚአብሔር በእኔ ላይ አይቈጣም!’ ትያለሽ፤ ነገር ግን ‘እኔ ኃጢአት አልሠራሁም’ ብለሽ በመካድሽ ምክንያት እኔ እግዚአብሔር እፈርድብሻለሁ።


“በዚያን ቀን መብራት ይዤ ኢየሩሳሌምን እፈትሻለሁ፤ በመንደላቀቅ ኑሮ በአተላ ውስጥ አቅርሮ እንደ ቀረ የወይን ጠጅ የሆኑትንና ‘እግዚአብሔር በጎም ሆነ ክፉ ነገር አያደርግም’ የሚሉትን እቀጣለሁ።


ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።


በዚያም ስትኖሩ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትናፍቃላችሁ፤ እርሱንም በሙሉ ልባችሁ ብትሹት ታገኙታላችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos