ኢዮብ 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአት ብሠራ አንተ ትመለከተኛለህ፥ ከኃጢአቴም ንጹሕ አታደርገኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአትን ብሠራ ትመለከተኛለህ፤ መተላለፌንም ሳትቀጣ አታልፍም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደል ብፈጽም አንተ ትመለከታለህ፤ ኃጢአቴንም ሳትቀጣ አታልፈውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢኣት ብሠራ አንተ ትጠባበቀኛለህ፤ ከኀጢኣቴም ንጹሕ አታደርገኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአት ብሠራ አንተ ትመለከተኛለህ፥ ከኃጢአቴም ንጹሕ አታደርገኝም። |
ፅኑ ፍቅሩን እስከ ሺህ ትውልድ የሚጠብቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በደለኛውን ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆችና በልጅ ልጆች ላይ እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ የሚያመጣ አምላክ ነው።”
‘ጌታ ታጋሽና ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ በደልንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን በደል እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።’