Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 16:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዓይኔ በመንገዶቻቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ከፊቴም አልተሰወሩም፥ ኃጢአታቸውም ከዓይኔ አልተሸሸገም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዐይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነው፤ በፊቴ የተገለጡ ናቸው፤ ኀጢአታቸውም ከዐይኔ የተሰወረ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የሚያደርጉትን ሁሉ አያለሁ፤ ከእኔ የሚሰወር ምንም ነገር የለም፤ ኃጢአታቸው ሁሉ በፊቴ የተገለጠ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዐይ​ኖች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ሁሉ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ከፊ​ቴም አል​ተ​ሰ​ወ​ሩም፤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ከዐ​ይ​ኖች አል​ተ​ሸ​ሸ​ገም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዓይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነው፥ ከፊቴም አልተሰወሩም፥ ኃጢአታቸውም ከዓይኔ አልተሸሸገም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 16:17
25 Referencias Cruzadas  

የጌታ ዐይኖች በስፍራ ሁሉ ናቸው፥ ክፉዎችንና ደጎችን ይመለከታሉ።


ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ይላል ጌታ። ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል ጌታ።


የሰው መንገድ በጌታ ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።


የተሰወረውን መተላለፋችንን በፊትህ ብርሃን፥ ምሥጢራችንን በፊትህ አስቀመጥህ።


በፊቱም የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ እኛ መልስ መስጠት በሚገባን ከእርሱ ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው።


ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።


በምክር ታላቅ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት ዐይኖችህ በአዳም ልጆች መንገድ ሁሉ ተገልጠዋል።


ጌታ ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ለማጽናት ዐይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና። እንግዲህ አሁን የሞኞችን ተግባር ፈጽመሃል። ስለዚህም ከዛሬ ጀምሮ ጦርነት ይደረግብሃል።”


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ኃጢአት እጅግ በዝቶአል፥ ምድሪቱ በደም ተሞልታለች፥ ከተማይቱም ዓመፅን ተሞልታለች፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ጌታ አያይም ብለዋልና።


ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከጌታ ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው!


ጉዞዬንና መኝታዬን አንተ መረመርህ፥ መንገዶቼን ሁሉ ቀድመህ አወቅህ፥


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”


በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፥ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።


በጌታ ፊት ሁልጊዜ ይኑሩ፥ መታሰቢያቸውም ከምድረ ገጽ ይጥፋ።


በእንዶድ ብትታጠቢም፥ ለራስሽም ሳሙናን አብዝተሽ ብትጠቀሚ እንኳ፥ በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በእስራኤል ዘንድ አሳፋሪ ነገር አድርገዋልና፤ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፤ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና፤ እኔም አውቀዋለሁ ምስክርም ነኝ፥ ይላል ጌታ።’ ”


በዚያም ዘመን ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ በአተላቸውም ላይ የሚረጉትን፥ በልባቸውም፦ “ጌታ መልካምም ክፉም አያደርግም” የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።


የዚህን የጥቂቱን ነገር ቀን የናቀ ማን ነው? በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን አይተው ይደሰታሉ። “እነዚህ ሰባቱም በምድር ሁሉ የሚዘዋወሩ የጌታ ዐይኖች ናቸው።”


ኃጢአት ብሠራ አንተ ትመለከተኛለህ፥ ከኃጢአቴም ንጹሕ አታደርገኝም።


መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?”


እርሱ ብቻውን ልባቸውን የሠራ ሥራቸውንም ሁሉ የሚያስተውል።


ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቃለሁ፤ አሕዛብንና ልሣናትን ሁሉ የምትሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፤ እነርሱም ይመጣሉ፥ ክብሬንም ያያሉ።


ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? እነሆ፥ እኔ ራሴ አይቻለሁ፥ ይላል ጌታ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios