ምግብ ሊበሉ ተቀመጡ፥ ዓይናቸውንም አንሥተው ሲያዩ፥ እነሆ የእስማኤላውያን ነጋዴዎች ወደ ግብጽ ለመውረድ ከገለዓድ ይመጣሉ፥ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን፥ ከርቤም ተጭነው ነበር።
ኤርምያስ 49:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንኳኖቻቸውንና መንጋቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ይወስዳሉ፤ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው እየነዱ ይወስዳሉ፥ እነርሱም፦ በዙሪያቸው ሁሉ ሽብር አለ፥ እያሉ ለእነርሱ ይጮኻሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንኳኖቻቸውና መንጎቻቸው ይወሰዳሉ፤ መጠለያቸውና ግመሎቻቸው ሳይቀሩ፣ ከነዕቃዎቻቸው ይነጠቃሉ፤ ሰዎች፣ ‘ሽብር በሽብር ላይ መጥቶባቸዋል፤’ እያሉ ይጮኹባቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንኳኖቻቸውን፥ መንጋዎቻቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ውሰዱ፤ ግመሎቻቸውን ለራሳችሁ ውሰዱ። ‘በዙሪያው ሽብር ተነሥቷል’ ብለው ይጮኻሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንኳናቸውንና በጎቻቸውን ይወስዳሉ፤ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ፥ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፤ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንኳናቸውንና መንጋቸውን ይወስዳሉ፥ መጋረጆቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ፥ በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው። |
ምግብ ሊበሉ ተቀመጡ፥ ዓይናቸውንም አንሥተው ሲያዩ፥ እነሆ የእስማኤላውያን ነጋዴዎች ወደ ግብጽ ለመውረድ ከገለዓድ ይመጣሉ፥ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን፥ ከርቤም ተጭነው ነበር።
ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።
የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።
ድንኳኔ ተበዘበዘ አውታሬም ሁሉ ተቈረጠ፤ ልጆቼም ከእኔ ወጥተው አይገኙም፤ ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።
ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኃያላኖቻቸውም ሲደበደቡ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዚህና በዚያ ድንጋጤ አለ፥ ይላል ጌታ።
እነሆ፥ በዙሪያሽ ካሉት ሁሉ ዘንድ በአንቺ ላይ ፍርሃትን አመጣብሻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትሰደዳላችሁ፥ የሚሸሹትንም የሚሰበስብ የለም።
ወደ መቄዶንያም በመጣን ጊዜ፥ በሁሉ ነገር መከራን ተቀበልን እንጂ ሰውነታችን ዕረፍት አልነበረውም፤ ከውጭ ጠብ ነበረ፤ ከውስጥ ደግሞ ፍርሃት ነበረብን።
ከብቶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው ሲመጡ ልክ የአንበጣ መንጋ ይመስሉ ነበር፤ ሰዎቹንም ሆነ ግመሎቻቸውን ለመቁጠር አዳጋች ሲሆን፥ የሚመጡትም ምድሪቱን ለማጥፋት ነበር።
ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም።
ዜባሕና ጻልሙናም፥ “የሰው ጉልበቱ እንደ ሰውነቱ መጠን ነውና፥ አንተው ራስህ ግደለን አሉት፤” ጌዴዎንም ተነሥቶ ገደላቸው፤ በግመሎቻቸው አንገት ላይ የነበሩትንም ጌጦች ወሰደ።
ሌሎቹን ጌጣ ጌጦች ይኸውም የአንገት ሐብሉን ከነእንጥልጥሉ፥ የምድያም ነገሥታት ይለብሱት የነበረውን ሐምራዊ ልብስ ወይም በግመሎቻቸው አንገት ላይ ያሉትን ጌጦች ሳይጨምር ጌዴዎን በጠየቃቸው መሠረት የሰጡት የወርቅ ጉትቻ ክብደት ሺህ ሰባት መቶ ሰቅል ያህል መዘነ።