Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 60:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የቄዳር የበግ መንጋ ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባል፤ የነባዮት አውራ በጎች ያገለግሉሻል። እነዚህም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው መሥዋዕቶች ይሆናሉ፤ እኔም የክብር መቅደሴን ግርማ አጐናጽፈዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የቄዳር የበግ መንጋዎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮት አውራ በጎችም ለመሥዋዕትነት ያገለግሉሻል፤ በመሠዊያም ላይ ለመሥዋዕትነት ለመቅረብ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። የተከበረውን ቤተ መቅደሴንም አስጌጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የቄ​ዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ የነ​ባ​ዮ​ትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይም የተ​መ​ረ​ጠው መሥ​ዋ​ዕት ይቀ​ር​ባል፤ የጸ​ሎቴ ቤትም ይከ​ብ​ራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፥ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 60:7
20 Referencias Cruzadas  

ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ።


በትውልዳቸው ቅደም ተከተል የተዘረዘሩት የእስማኤል የልጆቹ ስም እንዲህ ነው፥ የእስማኤል የበኩር ልጁ ነባዮት፥ እና ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥


በእግዚአብሔር ወንጌል እንደ ካህን እያገለገልሁ፥ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ እንድሆን ነው፥ ይህም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው የተወደደ መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።


አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችና ሰባት አውራ በጎች ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፥ የሚቃጠልንም መሥዋዕት ስለ ራሳችሁ አሳርጉ፥ አገልጋዬም ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል፥ እኔም እንደ ጥፋታችሁ እንዳላደርግባችሁ ጸሎቱን እሰማለሁ፥ እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና።”


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ሰውነታችሁን ሕያው መሥዋዕት፥ ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ አድርጋችሁ እንድታቀርቡ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም መንፈሳዊ አገልግሎታችሁ ነው።


ምድረ በዳውና ከተሞቹ የቄዳርም ሰዎች የሚቀመጡባቸው መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በሴላ የሚኖሩ እልል ይበሉ፥ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።


መሠዊያ አለን፤ ሆኖም ድንኳኒቱን የሚያገለግሉ ከእርሱ የመብላት መብት የላቸውም።


የመቅደሴንም ስፍራ ለማስጌጥ የሊባኖስ ክብር፥ ጥዱና አስታው፥ ባርሰነቱም ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።


መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፥ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ውብም ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።


በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለጌታ መሠዊያ ይሠራል፤ በድንበሯም ለጌታ ዓምድ ይቆማል።


በዚያም ቀን ጌታ ለግብጻዊያን ራሱን ይገልጣል፤ ግብጻውያንም ጌታን ያውቃሉ፤ በመሥዋዕትና በእህል ቁርባንም ያመልኩታል፤ ለጌታም ስእለት ይሳላሉ፤ የተሳሉትንም ይፈጽማሉ።


ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤


በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው በምድሩ ላይ ያመልኩኛል፤ በዚያም እቀበላቸዋለሁ፥ በዚያም ቁርባናችሁን በኩራታችሁንም የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ እፈልጋለሁ።


ዓረብና የቄዳር ልዑላን ሁሉ የእጅሽ ነጋዴዎች ነበሩ፤ በጠቦቶች፥ በአውራ በጎችና በፍየሎች በእነዚህ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር።


ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚያመልኩኝ፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቁርባኔን ያመጡልኛል።


“ሩጥ፥ ይህንም ጎልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ትሆናለች።


እንዲህም ይሆናል፥ በመጨረሻው ዘመን የጌታ ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶች በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios