አሜስያስ “የጨው ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላዕ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች።
ኤርምያስ 49:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ በዐለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውንም ከፍታ የያዝህ ሆይ፤ የምትነዛው ሽብር፣ የልብህም ኵራት አታልሎሃል፤ መኖሪያህን እስከ ንስር ከፍታ ቦታ ብትሠራም፣ ከዚያ ወደ ታች አወርድሃለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አለታማው ገደል ላይ የምትኖሪ፥ እስከ ተራራማው ጫፍ ድረስ የምትደርሽ ሆይ! ተፈሪነትሽና የልብሽ ኲራት አታለውሻል፤ ምንም እንኳ መኖሪያሽን እንደ ንስር ጎጆ ብታደርጊ እኔ ከዚያ ላይ አወርድሻለሁ ይላል እግዚአብሔር።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ድፍረትህና የልብህ ኵራት አነሣሥተውሃል። ቤትህንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ፥ ድፍረትህና የልብህ ኵራት አታልለውሃል። ቤትህን ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
አሜስያስ “የጨው ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላዕ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ “ዮቅትኤል” ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች።
ሰው እጁን ወደ ወፍ ጎጆ እንደሚሰድ፤ እኔም እንዲሁ እጄን ወደ መንግሥታት ሀብት ሰደድሁ፤ ሰዎች የተተወ ዕንቁላል እንደሚሰበስቡ፤ እኔም እንዲሁ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ፤ ክንፉን ያራገበ የለም፤ አፉንም ከፍቶ የጮኸ አልነበረም።’”
ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፤ ወደ ድንጋይ ዋሻ፤ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።
ጌታ ግን እንዲህ ይላል፦ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፥ ልጆችሽንም አድናለሁና፥ በኃያላን የተማረኩ እንኳን ይወሰዳሉ፥ የጨካኞች ብዝበዛም ቢሆን ያመልጣል።
ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።