Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማሕልየ መሓልይ 2:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ድምፅሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አንቺ በገደል ዐለት ንቃቃት፣ በተራሮችም ባሉ መደበቂያ ስፍራዎች ውስጥ ያለሽ ርግቤ ሆይ! ፊትሽን አሳዪኝ፤ ድምፅሽንም አሰሚኝ፤ ድምፅሽ ጣፋጭ፣ መልክሽም ውብ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አንቺ በገደል አለት ንቃቃት ውስጥ እንደ ተደበቀች ርግብ ነሽ፤ እስቲ አንድ ጊዜ ፊትሽን ልየው፤ ድምፅሽንም ልስማው፤ ድምፅሽ አስደሳች ነው፤ ፊትሽም እጅግ የተዋበ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ቃልሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ።

Ver Capítulo Copiar




ማሕልየ መሓልይ 2:14
41 Referencias Cruzadas  

ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን ሰማ ብዬ አላምንም ነበር።


ግርማዊ ክብር ከልደትህ ጊዜ አንሥቶ፥ የተቀደሰ ሞገስም ከማኅጸን፥ የወጣትነትም ጠል የአንተ ነው።


አምላኬ፥ በቀን ወደ አንተ እጠራለሁ፥ አልመለስህልኝም፥ በሌሊትም እንኳ ዕረፍት የለኝም።


ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ፥ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፥


ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና እጅ ንሺው።


ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል፥ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።


የሠራዊት ነገሥታት ፈጥነው ይሸሻሉ፥ በቤትም የምትኖር ምርኮን ተካፈለች።


የምትገዛልህን እርግብ ለአራዊት አትስጣት፥ የችግረኞችህን ነፍስ መቼውንም አትርሳ።


እርሱም፦ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ማየት ፈርቶ ፊቱን ሸፈነ።


የኀጥኣን መሥዋዕት በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ፥ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ ዐይኖችሽም እርግቦች ናቸው።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ውብም ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።


አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ያላወቅሽ እንደሆነ የመንጎችን ፍለጋ ተከትለሽ ውጪ፥ የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞች ድንኳኖች አጠገብ አሰማሪ።


እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ድምፅ ነው፥ እርሱም ያንኳኳል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ፥ ራሴ በጠል፥ ጸጉሬም በሌሊት ነጠብጣብ ርሶአል።


በገነቱ የምትቀመጪ ሆይ፥ ባልንጀሮች የአንቺን ድምፅ ይሰማሉ፥ ድምፅሽን አሰሚኝ።


ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፤ ወደ ድንጋይ ዋሻ፤ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።


ጌታም ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርሷም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፤ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔድን በረሀዋንም እንደ ጌታ ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።


እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።


ርግቦች ወደ ጎጇቸው እንደሚበርሩ፥ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው?


እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ! ከተሞችን ትታችሁ በዓለት ንቃቃት መካከል ተቀመጡ፥ በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ።


በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።


ከእነርሱም የሚሸሹ ያመልጣሉ፥ እንደ ሸለቆ እርግቦች በተራራ ላይ ይሆናሉ፥ ሁሉም በኃጢአታቸው ላይ ያቃስታሉ።


በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ የምትኖር፥ ማደሪያህንም ከፍ ከፍ ያደረግህ፥ በልብህም፦ ወደ ምድር የሚያወርደኝ ማን ነው? የምትል አንተ ሆይ፥ የልብህ ትዕቢት አታልሎሃል።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ ከውኃ ወጣ፤ እነሆ ሰማያት ተከፈቱ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየ፤


እንዲሁም ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም አንዳች እንከን ሳይገኝባት ቅድስትና ነውር የሌለባት አድርጎ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያንን ለራሱ ሊያቀርባ እንደፈለገ፥


አሁን በእርሱ ፊት ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ቅዱሳን አድርጎ ለማቅረብ በሥጋዊው አካሉ በሞቱ አስታረቃችሁ።


ከክፉ ኅሊና ለመንጻት ልባችንን ተረጭተንና ሰውነታችንን በንጹህ ውሃ ታጥበን፥ በቅን ልብ በፍጹም እምነት እንቅረብ፤


እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ፥ ጸጋው ወደሚገኝበት በመታመን እንቅረብ።


ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጽሞና መንፈስ የተዋበው የተሰወረ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።


አሁንም ሳትሰናከሉ ሊጠብቃችሁ፥ በክብሩ ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ ሊያቆማችሁ ለሚችለው፤


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሳሕን ያዙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos