Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 39:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ንስር ከፍ ከፍ የሚለው፥ ቤቱንም በከፍታ ላይ የሚያደርገው በአንተ ተእዛዝ ነውን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ንስር ወደ ላይ የሚመጥቀው፣ ጐጆውንም በከፍታ ላይ የሚሠራው፣ በአንተ ትእዛዝ ነውን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ንስርን ወደ ላይ ወጥቶ በከፍተኛም ቦታ ላይ ጎጆውን የሚሠራው አንተ አዘኸው ነውን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በአ​ፍህ ትእ​ዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላ​ልን? ጆፌ አሞ​ራስ ልጆ​ቹን አቅፎ ያድ​ራ​ልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በአፍህ ትእዛዝ ንስር ከፍ ከፍ ይላልን? ቤቱንስ በአርያም ላይ ያደርጋልን?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 39:27
11 Referencias Cruzadas  

እንደ ንስር መጥቀህ ብትወጣ፥ ቤትህም በከዋክብት መካከል ቢሆን፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።


በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ማሣቀቅያህና የልብህ ኩራት አታልለውሃል። ምንም እንኳ ጎጆህን እንደ ንስር ጎጆ ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥ ይላል ጌታ።


በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንዴት እንደ ተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።


መለከትን ወደ አፍህ አቅርብ፤ ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና እንደ ንስር በጌታ ቤት ላይ እያንዣበበ ነው።


ጌታን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።


ቀና ብለህ እያየኸው ይጠፋል፥ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና።


ምኞትሽን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጎልማሳነትሽን እንደ ንስር ያድሳል።


“ከወፎችም ወገን የምትጸየፉአቸው እነዚህ ናቸው፤ አይበሉም፤ የተጸየፉ ናቸው፤ ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጭ፥


በውኑ ጭልፊት የሚያንዣብበው፥ ክንፎቹንስ ወደ ደቡብ የሚዘረጋው በአንተ ጥበብ ነውን?


የሌሊት መኖርያው ዓለት ነው፥ የዓለት ጫፍም መከላከያ ይሆነዋል።


እነርሱም የንስር መንገድ በሰማይ፥ የእባብ መንገድ በድንጋይ ላይ፥ የመርከብ መንገድ በባሕር ላይ፥ የሰውም መንገድ ከቈንጆ ጋር ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios