La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 49:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የመሸሸጊያውንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ እርሱም ለመሸሸግ አይችልም፤ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ ግን ዔሳውን አራቍተዋለሁ፤ መደበቅም እንዳይችል፣ መሸሸጊያ ስፍራዎቹን እገልጣለሁ፤ ልጆቹ፣ ዘመዶቹና ጎረቤቶቹ ይጠፋሉ፤ እርሱም ራሱ አይኖርም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ ግን የዔሳውን ዘር በፍጹም አራቊታቸዋለሁ። የሚሸሸጉበትንም ስፍራ አጋልጣለሁ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ የሚሸሸጉበት ስፍራ ማግኘት አይችሉም፤ ልጆቻቸው፥ ዘመዶቻቸውና ጐረቤቶቻቸው ይጠፋሉ፤ እነርሱም አይኖሩም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ ግን ዔሳ​ውን አራ​ቆ​ት​ሁት፤ የተ​ሸ​ሸ​ጉ​ት​ንም ስፍ​ራ​ዎች ገለ​ጥሁ፤ ይሸ​ሸ​ግም ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ዘሩም፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፤ ጎረ​ቤ​ቶ​ቹም ጠፍ​ተ​ዋል፥ እር​ሱም የለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የተሸሸጉትንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ ይሸሸግም ዘንድ አይችልም፥ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 49:10
13 Referencias Cruzadas  

ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


በመሸ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሽብር አለ! ከመንጋቱም በፊት አንዳቸውም አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች እድል ፈንታ፥ የበዘበዙንም ዕጣ ይህ ነው።


በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።


ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።


ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ይላል ጌታ። ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል ጌታ።


ታው። የጽዮን ልጅ ሆይ፥ የበደልሽ ቅጣት ተፈጸመ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም። የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ በደልሽን ይቀጣል፥ ኃጢአትሽን ይገልጣል።


በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤


ዔሳው ምንኛ ተበረበረ! ብርቅዬ ሀብቱ ምንኛ ተፈለገ!


ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ በግድያ እንዲጠፉ ኃያላን ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ።


“ያዕቆብን ወደድሁ፥ ኤሳውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።