Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




አብድዩ 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ በግድያ እንዲጠፉ ኃያላን ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ቴማን ሆይ፤ ተዋጊዎችህ ይደነግጣሉ፤ በዔሳውም ተራሮች ያለ ሁሉ፣ ተገድሎ ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በኤዶም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይገደላሉ፤ የቴማንም ጀገኖች በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ከዔ​ሳው ተራራ ሰዎች ሁሉ ይጠፉ ዘንድ የቴ​ማን ሰል​ፈ​ኞ​ችህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ቴማን ሆይ፥ ሰዎች ሁሉ ከዔሳው ተራራ በመገደል ይጠፉ ዘንድ ኃያላንህ ይደነግጣሉ።

Ver Capítulo Copiar




አብድዩ 1:9
19 Referencias Cruzadas  

በቴማን ላይ እሳትን እልካለሁ፥ የባሶራንም የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች።”


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኤዶምያስ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፥ ከእርሷም ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ ባድማ አደርጋታለሁ፤ ከቴማን ጀምሮ እስከ ድዳን ድረስ በሰይፍ ይወድቃሉ።


እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።”


የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጋታም፥ ቄናዝ።


ስለዚህ ጌታ በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያቸውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል።


ስለ ኤዶምያስ፤ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?


ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።


በዔሳውም ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ አዳኞች ወደ ጽዮን ተራራ ላይ ይወጣሉ፥ መንግሥቱም ለጌታ ይሆናል።


በዚያ ቀን በኃያላኑም መካከል ልበ ሙሉው ዕራቁቱን ሆኖ ይሸሻል፥” ይላል ጌታ።


ኢዮባብም ሞተ፥ በእርሱም ፋንታ የቴማን አገር ሰው ሑሳም ነገሠ።


እነሆ፥ በመካከልሽ ያለው ሕዝብሽ ሴቶች ናቸው፤ የምድርሽ በሮች ለጠላቶችሽ በሰፊው ተከፍተዋል፥ መወርወሪያዎችሽን እሳት በልቶአቸዋል።


የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።


ሌቦች ቢመጡብህ ወይም ወንበዴዎች በሌሊት ቢመጡ፥ የሚበቃቸውን ብቻ ይሰርቁ የለምን? ወይንንም የሚቆርጡ ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ ያስቀሩ የለምን? አንተ ግን ምንኛ ጠፋህ!


እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፓራን ተራራ መጣ። (ሴላ) ውበቱ ሰማያትን ሸፍኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios