ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
ኤርምያስ 46:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ውርደትሽን ሰምተዋል፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቦች ኀፍረትሽን ይሰማሉ፤ ልቅሶሽም ምድርን ይሞላል። ጦረኛ በጦረኛው ይደናቀፋል፤ ሁለቱም ተያይዘው ይወድቃሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦች ሁሉ ስለ ኀፍረትሽ ሰምተዋል፤ የዓለምም ሕዝብ ሁሉ ጩኸትሽን አድምጠዋል፤ አንዱ ወታደር ሌላውን ወታደር ሲያደናቅፈው ሁሉም ተያይዞ መሬት ይወድቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጦረኞች በጦረኞች ላይ ተሰናክለው ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ቃልሽን ሰምተዋል፤ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያሉ በኃያሉ ላይ ተሰናክሎ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ ጕስቍልናሽን ሰምተዋል፥ ልቅሶሽም ምድርን ሞልቶአታል። |
ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
“ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ውኃ ከሰሜን ይነሣል የሚያጥለቀልቅም ጐርፍ ይሆናል፤ በአገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
ከሐሴቦን ጮኹ እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን አሰሙ፤ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ደርሶአል፤ የኔምሬም ውኃ ደግሞ ይደርቃል።