ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ ትእዛዛቴን ብትጠብቁ ብትፈጽሟቸውም፥ ከእናንተ ውስጥ የሆኑ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜ እንዲኖርበት ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።”
ኤርምያስ 36:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናልባት የይሁዳ ቤት እኔ ላደርግባቸው ያሰብኩትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል፥ ከዚህም የተነሣ ሁላቸውም ከክፉ መንገዳቸው ተመልሰው በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምናልባትም የይሁዳ ሕዝብ ላመጣባቸው ያሰብሁትን ጥፋት ሁሉ ሲሰሙ፣ እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ክፋታቸውንና ኀጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ በእነርሱ ላይ ላመጣ ያቀድኩትን ጥፋት በሚሰሙበት ጊዜ ምናልባት ከክፉ ሥራቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናልባት የይሁዳ ቤት ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ዘንድ፥ እኔም በደላቸውንና ኀጢአታቸውን ይቅር እል ዘንድ፥ እኔ አደርግባቸዋለሁ ያልሁትንና ያሰብሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምናልባት የይሁዳ ቤት፦ እኔ አደርግባቸዋለሁ ያልሁትንና ያሰብሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል፥ ከክፋ መንገዳቸው ይመለሱ ዘንድ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ዘንድ። |
ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ ትእዛዛቴን ብትጠብቁ ብትፈጽሟቸውም፥ ከእናንተ ውስጥ የሆኑ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜ እንዲኖርበት ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።”
የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ ጆሮአቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ ይህ ካልሆነማ፤ በዐይናቸው አይተው፤ በጆሮአቸው ሰምተው፤ በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።”
አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚቀመጡ፦ ‘ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፥ አሳብንም አስብባችኋለሁ፤ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አስተካክሉ’ ብለህ ተናገራቸው።
በኢየሩሳሌምም ነቢያት መካከል አስደንጋጭ ነገር አይቻለሁ፤ ያመነዝራሉ በሐሰትም ይሄዳሉ፤ ማንም ከክፋቱ እንዳይመለስ የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ሁላቸውም እንደ ሰዶም የሚኖሩባትም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ።
እንዲሁም፦ ‘እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፥ ሥራችሁንም አሳምሩ፥ ልታገለግሉአቸውም ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፥ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ’ እያልሁ በማለዳ ተነሥቼ ባርያዎቼን ነቢያትን ሁሉ ላክሁባችሁ፤ ላክሁ፥ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም እኔንም አልሰማችሁኝም።
ጌታ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በጌታ ፊት ይቀርብ ይሆናል፥ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።”
አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የስደተኛ ጓዝ ለራስህ አዘጋጅ፥ እያዩህም በቀን ወደ ምርኮ ሂድ፥ በፊታቸውም እንደ ምርኮኛ ከስፍራህ ወደ ሌላ ስፍራ ሂድ፥ ዓመፀኛ ቤት ቢሆኑም ምናልባት ያስተውሉ ይሆናል።
እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ፥ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ ጌታን ፈልጉ፤ ጽድቅን ፈልጉ፥ ትሕትናን ፈልጉ፤ ምናልባት በጌታ ቁጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።
በዓይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ተመልሰው እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፥ ጆሮአቸው ደንቁሮአል፥ ዓይናቸውም ተጨፍኖአል፤
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሓ ይገቡ ዘንድና ለንስሓ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ተናገርሁ።
በዐይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዐይናቸውንም ጨፍነዋል፤ በላቸው።
እንግዲህ ከጌታ ፊት የመጽናናት ዘመን እንድትመጣላችሁ አስቀድሞም ለእናንተ የመረጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲልክላችሁ፥ ኀጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ ንስሐ ግቡ፤ ተመለሱም።
እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!
አንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው፥ ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በፍጹም ልባችሁ ወደ ጌታ የምትመለሱ ከሆነ፥ ባዕዳን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለጌታ አሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋችኋል።” አላቸው።