ኢሳይያስ 66:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወጥተው ሲሄዱም በእኔ ላይ በማመፃቸው የተገደሉትን ሰዎች በድን ያያሉ፤ እነርሱን የሚበላቸው ትል አይሞትም፤ የሚያቃጥላቸውም እሳት አይጠፋም፤ እነርሱንም የሚያያቸው የሰው ዘር ሁሉ ይጸየፋቸዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትም፤ እሳታቸውም አይጠፋም፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆናሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፥ ትላቸው አይሞትምና፥ እሳታቸውም አይጠፋምና፥ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ። |
በሌሊትና በቀንም አትጠፋም፤ ጢስዋም ለዘለዓለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለዘለዓለም ዓለም ማንም አያልፍባትም።
የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
ጌታም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፤ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዐይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
ነገር ግን የሚፈሩ፥ የማያምኑ፥ የሚረክሱ፥ ነፍሰ የሚያጠፉ፥ የሚሴሰኑ፥ አስማትን የሚያደርጉ፥ ጣዖትንም የሚያመልኩና የሚዋሹ ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”