Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 65:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስማችሁንም ለተመረጡት ሕዝቤ እርግማን አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፥ ጌታ እግዚአብሔርም ይገድላችኋል፥ አገልጋዮቹንም በሌላ ስም ይጠራቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስማችሁንም፣ የተመረጠው ሕዝቤ ርግማን እንዲያደርገው ትተዋላችሁ፤ ጌታ እግዚአብሔር ይገድላችኋል፤ ለአገልጋዮቹ ግን ሌላ ስም ይሰጣቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እኔ ጌታ እግዚአብሔርም እናንተን ለሞት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የእናንተም ስም በእኔ ተመራጮች ዘንድ መራገሚያ ይሆናል፤ ለአገልጋዮቼ ግን የተለየ ስም እሰጣቸዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስማ​ች​ሁ​ንም እኔ ለመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድ​ር​ጋ​ችሁ ትተ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ች​ኋል፤ ባሪ​ያ​ዎች ግን በሐ​ዲስ ስም ይጠ​ራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስማችሁንም ለተመረጡት ሕዝቤ እርግማን አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፥ ጌታ እግዚአብሔርም ይገድላችኋል፥ ባሪያዎቹንም በሌላ ስም ይጠራቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 65:15
23 Referencias Cruzadas  

ነቅቼ፥ በሰገነትም እንደሚኖር ብቸኛ ድንቢጥ ሆንሁ።


የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው፥ የክፉ ስም ግን ይጠፋል።


አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የጌታም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።


እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ፥ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጋችሁ፥ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራኋችሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝም፤ በተናገርኩም ጊዜ አልሰማችሁኝም።


ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።


ከያዕቆብም ዘርን ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤ እኔም የመረጥኳቸው ይወርሷታል፥ አገልጋዬቼም በዚያ ይኖራሉ።


እነሆ፥ ጌታ መዓቱን በቁጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።


በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆናሉ፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤና ለክፉ ነገር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ባድማና መሣቀቂያ ማፍዋጫም እርግማንም ላደርጋቸው፥ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ነገሥታትዋንም አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።


ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፥ ይህችንም ከተማ ለምድር አሕዛብ ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።’ ”


በሰይፍም በራብም በቸነፈርም አሳዳድዳቸዋለሁ፤ ባሳደድኋቸውም አሕዛብ ሁሉ መካከል ለመረገሚያና ለመሣቀቂያ ለማፍዋጫም ለመሰደቢያም ይሆናሉ፤ በምድር መንግሥታትም ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


ከእነርሱም የተነሣ በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ ይህን እርግማን ይጠቀማሉ፥ እንዲህም ይላሉ፦ “የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ጌታ ያድርግህ፥”


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ተናግሮአልና፦ ቁጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ወረደ፥ እንዲሁ ወደ ግብጽ በገባችሁ ጊዜ መዓቴ ይወርድባችኋል፤ እናንተም ለጥላቻና ለመሣቀቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ትሆናላችሁ፥ ይህንም ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም።


ወደ ግብጽም ለመግባት በዚያም ለመቀመጥ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ትሩፍ እወስዳለሁ፥ ሁሉም ይጠፋሉ፥ በግብጽም ምድር ይወድቃሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለመሣቀቂያ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።


ፊቴን በዚያ ሰው ላይ አደርጋለሁ ምልክትና ምሳሌም አደርገዋለሁ፥ ከሕዝቤም መካከል አስወግደዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ በረከት መሆን እንድትችሉ አድናችኋለሁ፤ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።


እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ሁኔታ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ሥፍራ ፍሬውን በየጊዜው ለሚሰጡት ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል” አሉት።


ንጉሡም ተቆጣ፤ ወታደሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።


ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው። በቤተ ክርስቲያንም አንድ ዓመት ሙሉ ተሰበሰቡ፤ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም መጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።


ደግሞም፥ ‘እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብሎ በተነገረላቸው ስፍራ፥ በዚያ ‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።” ይላል።


ለአሕዛብ እንዳንናገር በመከልከል እነርሱ እንዳይድኑ ያደርጋሉ፤ በዚህም ያለማቋረጥ የኃጢአታቸውን መስፈርያ ይሞላሉ፤ ነገር ግን በመጨረሻ የእግዚአብሔር ቁጣው ይመጣባቸዋል።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም ተጽፎአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos