ኢሳይያስ 65:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ፥ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጋችሁ፥ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራኋችሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝም፤ በተናገርኩም ጊዜ አልሰማችሁኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተጣርቼ ስላልመለሳችሁ፣ ተናግሬ ስላልሰማችሁ፣ በፊቴ ክፉ ነገር ስላደረጋችሁ፣ የሚያስከፋኝን ነገር ስለ መረጣችሁ፣ ለሰይፍ እዳርጋችኋለሁ፤ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እናንተ በጠራኋችሁ ጊዜ መልስ ስላልሰጣችሁና በተናገርኩም ጊዜ ስላላዳመጣችሁ ለእኔ መታዘዝን ትታችሁ ክፉ ማድረግን ስለ መረጣችሁ ዕድል ፈንታችሁ ለገዳይ ተንበርክኮ በሰይፍ መገደል ይሆናል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ሁላችሁም በሰይፍ ትገደላላችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደረጋችሁ፤ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራኋችሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰማችሁኝምና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ፥ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ፥ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጋችሁ፥ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰማችሁኝምና። |
ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።
ጌታ መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና፥ የጌታ ሰይፍ በደም ትርሳለች፤ ስብ ትጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ኩላሊት ስብ ትወፍራለች።
በመጣሁስ ጊዜ ሰው ስለምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝም? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፥ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም አጥተው ዓሦቻቸው ይገማሉ፥ በጥማትም ይሞታሉ።
ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፥ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፥ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፥ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፥ ጉልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
“ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው የአርነት አዋጅ ለመንገር እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ፥ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር ለራብም የአርነት አዋጅ እናገርባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምድር መንግሥታትም ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሆነ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፥ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና በእነርሱ ላይ የተናገርኩትን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በተቀመጡ ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።”
አሁንም እነዚህን ነገሮች ሁሉ ስላደረጋችሁ፥ ይላል ጌታ፥ በማለዳም ተነሥቼ ባለማቋረጥ በተናገርኋችሁ ጊዜ ስላልሰማችሁ፥ በጠራኋችሁም ጊዜ ስላልመለሳችሁ፥
የቃል ኪዳኑንም በቀል የሚበቀል ሰይፍ አመጣባችኋለሁ፤ ወደ ከተሞቻችሁም ትሰበሰባላችሁ፥ በመካከላችሁም ቸነፈርን እልክባችኋለሁ፤ በጠላትም እጅ ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ።
ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች እየኖሩባቸው፥ በሰላም ተቀምጠው እያሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች እየኖሩባቸው በነበረ ጊዜ አይደለም እንዴ፥ ይህንን ቃል ጌታ በቀደሙት ነቢያት አማካኝነት የተናገረው?