እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።
ኢሳይያስ 62:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል ጌታንም ያመሰግናሉ፥ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል ብሎ በቀኙና በኃይሉ ክንድ ምሏል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን መከሩን የሰበሰቡ ይበሉታል፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፤ የወይኑን ፍሬ የለቀሙም በመቅደሴ አደባባዮች ይጠጡታል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በጐተራ የሰበሰቡትን እህል እነርሱ ራሳቸው በልተው እኔ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ የሰበሰቡትንም የወይን ዘለላ የወይን ጠጅ እነርሱ ራሳቸው በተቀደሰ አደባባዬ ይጠጡታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፤ ያከማቹትንም ወይን በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፥ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል ብሎ በቀኙና በኃይሉ ክንድ ምሎአል። |
እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ይበላሉ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ደስ ይላቸዋል እናንተ ግን ታፍራላችሁ፤
ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።
ብዙ መብል ትበላላችሁ፥ ትጠግቡማላችሁ፥ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የጌታ የአምላካችሁን ስም ታመሰግናላችሁ፥ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም።
“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፤ እኔም በዚህ ስፍራ ከቆሙት ጋር ስፍራን እሰጥሃለሁ።”
እዚያም እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም የራሳቸው ድርሻ ወይም ርስት የሌላቸው በየከተሞቻችሁ የሚኖሩት ሌዋውያን በጌታ በአምላካችሁ ፊት ሐሤት አድርጉ።”
በዚያም በጌታ በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፤ ጌታ አምላካችሁ እናንተን በባረከበት፥ በምታደርጉት ሁሉ አንተና ቤተሰቦችህ ሐሤት ታደርጋላችሁ።”
አንተ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችህ፥ በከተሞችህ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ በመካከልህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች ጌታ እግዚአብሔር ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባርያህና ሴት ባርያህ፥ በአገርህም ደጅ ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሀ አደግና መበለትም በበዓል ደስ ይበላችሁ።