Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 62:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጌታ፦ ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እግዚአብሔር በቀኝ እጁ፣ በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሏል፤ “ከእንግዲህ እህልሽን፣ ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤ ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣ አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር በኃይሉና በሥልጣኑ እንዲህ ሲል ማለ፦ “ከእንግዲህ ወዲያ እህልሽን ጠላቶችሽ እንዲበሉት አላደርግም፤ የደከምሽበትን አዲስ የወይን ጠጅሽንም ባዕዳን እንዲጠጡት አላደርግም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በእ​ር​ግጥ ለጠ​ላ​ቶ​ችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህ​ል​ሽን አል​ሰ​ጥም፥ መጻ​ተ​ኞ​ችም የደ​ከ​ም​ሽ​በ​ትን ወይ​ን​ሽን አይ​ጠ​ጡም፤” ብሎ በጌ​ት​ነ​ቱና በክ​ንዱ ኀይል ምሎ​አል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እግዚአብሔር፦ ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 62:8
16 Referencias Cruzadas  

የምድርህንና የድካምህን ፍሬ ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል። ዕድሜ ልክህን በጭካኔና በማያቋርጥ ጭቆና ትኖራለህ።


በሬህ ዐይንህ እያየ ይታረዳል፤ አንዳች ግን አትቀምሰውም። አህያህም በግድ ይወሰድብሃል፤ ለአንተም አይመለስልህም። በጎችህ ለጠላቶችህ ይሰጣሉ፤ የሚረዳህ ማንም አይኖርም።


እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤልን በመረጥሁበት ቀን፥ ለያዕቆብ ቤት ዘር ማልሁላቸው፥ በግብጽም ምድር ራሴን ገለጥሁላቸው፦ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ ብዬ ማልሁላቸው።


መከርህንና እንጀራህን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህንም ይበሉአቸዋል፤ በጎችህንና ላሞችህንም ይበላሉ፤ ወይንህንና በለስህንም ይበላሉ፤ የምትተማመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደመስሳሉ።


አገራችሁ ባድማ፤ ከተሞቻችሁ በእሳት የተቃጠሉ ይሆናሉ፤ ዐይናችሁ እያየ መሬታችሁ በባዕድ ይነጠቃል፤ ጠፍም ይሆናል።


እጄን ወደ ሰማይ ዘርግቼ፥ ለዘለዓለም እኔ ሕያው እንደሆንኩ፥ እምላለሁ።


እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ነፍስን የሚያኮስስና ዓይንን የሚያፈዝዝ ክሳትና ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ይበሉታልና ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።


ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም፦ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።


ይህ ለኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ።


እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።


“ሚስት ለማግባት ታጫለህ፤ ሌላም ሰው ከእርሷ ጋር ይተኛል። ቤት ትሠራለህ፥ ግን አትኖርበትም። ወይን ትተክላለህ፤ ፍሬውን ግን አትበላም።


ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ የራሱም ጽድቅ ደገፈው።


እንደገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ ወይንን በወይን እርሻዎች ትተክዪአለሽ፤ አትክልተኞች ይተክላሉ እነርሱም በፍሬው ይደሰታሉ።


የሕዝቤን የእስራኤልን ምርኮ እመልሳለሁ፥ የፈረሱትንም ከተሞች ዳግም ሠርተው ይቀመጡባቸዋል፤ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁንም ይጠጣሉ፤ የአትክልት ስፍራዎችንም ያበጃሉ፥ ፍሬውንም ይበላሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios