ኢሳይያስ 51:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ! ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር እጅ፣ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ፣ ዝቃጩ እንኳ ሳይቀር፣ ሰዎችን የሚያንገደግደውን ዋንጫ የጨለጥሽ፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ተነሺ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንቺ ከእግዚአብሔር እጅ የሚያንገዳግደውን የቊጣውን ጽዋ በትልቅ ዋንጫ ጨልጠሽ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ንቂ፤ ተነሥተሽም ቁሚ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚያንገደግድሽን የቍጣውን ጽዋ ጠጥተሻልና፥ ጨልጠሽውማልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ፥ ቁሚ፥ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል። |
ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ፤ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፥ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፥ ከጌታም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርሷ ጩኹ።
ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።
የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።
አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት ካህናቱንም ነቢያቱንም በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።
ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ባድማና መሣቀቂያ ማፍዋጫም እርግማንም ላደርጋቸው፥ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች ነገሥታትዋንም አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።
አንተም፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምልከው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፥ ስከሩም፥ አስታውኩም፥ ውደቁም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው።
እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የሚያንገዳግድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ ደግሞም ይሁዳ እንደተከበበች ኢየሩሳሌም እንዲሁ ትከበባለች።
እርሱ ደግሞ በቁጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር የቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።
ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንዲሰጣትም ታላቂቱ ባቢሎን በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።