ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በዚያ የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው ሁሉንም ፈጽመው እስከሚያጠፏቸው ድረስ ሐውልቶቹን ሰባበሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጡ፥ በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኮረብታው መስገጃዎችና መሠዊያዎች አፈረሱ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።
ኢሳይያስ 30:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን፥ በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ “ከእኔ ራቁ!” ትላቸዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በብር የተለበጡትን ጣዖቶችህንና በወርቅ የተለበዱ ምስሎችህን ታዋርዳለህ፤ “ከዚህ ወግዱ!” ብለህም እንደ መርገም ጨርቅ ትጥላቸዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በብርና በወርቅ የተለበጡትን ጣዖቶቻችሁንም “ከእኛ ወዲያ ራቁ!” ብላችሁ በመጮኽ እንደ ረከሰ ነገር አሽቀንጥራችሁ ትጥሉአቸዋላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብርም ወደ ተለበጡ፥ በወርቅም ወደ አጌጡ ወደ ጣዖታቱ እንሂድ የሚሉ ናቸው፤ ያንጊዜ እንደ ትቢያ የደቀቁ ይሆናሉ፤ እንደ ውኃም ይደፈርሳሉ፤ በእነርሱም ጥራጊዎችን ይጥሉባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፥ እንደ ርኩስም ነገር ትጥላቸዋለህ፦ ወግዱ ትላቸውማለህ። |
ይህም ሁሉ በተፈጸመ ጊዜ በዚያ የተገኙ እስራኤል ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው ሁሉንም ፈጽመው እስከሚያጠፏቸው ድረስ ሐውልቶቹን ሰባበሩ፥ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቈረጡ፥ በይሁዳና በብንያምም ሁሉ ደግሞም በኤፍሬምና በምናሴ የነበሩትን የኮረብታው መስገጃዎችና መሠዊያዎች አፈረሱ። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስታቸውና ወደ ከተሞቻቸው ተመለሱ።
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ነው።
ወርቁን ከኮሮጆ የሚያፈስሱ፥ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፤ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል።
ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች የሚያጽናናት የለም፥ እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉትን እንዲያስጨንቁት አዘዘ፥ ኢየሩሳሌም በመካከላቸው እንደ ርኩስ ነገር ሆናለች።
ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመለሱ፥ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ።
ብራቸውን በጎዳናዎቹ ላይ ይጥላሉ፥ ወርቃቸውም እንደ ርኩስ ነገር ይቆጠራል፥ በጌታ የመዓት ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም። አይጠግቡም፥ ሆዳቸውንም አይሞሉም፥ የኃጢአታቸው ዕንቅፋት ሆኖአልና።
የጌጦቻቸውን ውበት ወደ ትዕቢት ለወጡ፥ የርኩሰታቸውን ምስሎችና አስከፊ ነገሮችን ሰሩባቸው፥ ስለዚህ እኔም ይህንን ለእነርሱ ርኩስ ነገር አደርገዋለሁ።
ከጥላውም በታች የሚቀመጡ ይመለሳሉ፤ እንደ አትክልት ስፍራ ይለመልማሉ፤ እንደ ወይንም ተክል ያብባሉ፤ መዓዛቸውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል።
ልብሱን ያቃጥል፤ ድሩ ወይም ማጉ የበግ ጠጉር ወይም በፍታ ወይም ከተለፋው ቆዳ የሆነ ማናቸውም ደዌው ያለበት ነገር ላይ ቢሆን፥ እየሰፋ የሚሄድ የለምጽ ደዌ ነውና በእሳት ይቃጠል።
በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ የጣዖታትን ስም ከምድር አጠፋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፤ ደግሞም ሐሰተኞችን ነቢያትና ርኩስ መንፈስን ከምድር ላይ አስወግዳለሁ።
የተቀረጸውንም የአምላኮቻቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላለህ፤ በእነርሱ ላይ የተለበጠውን ብር ወይም ወርቅ አትመኝ፥ በጌታ አምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመድበት ከእርሱ ምንም አትውሰድ።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።