ኢሳይያስ 3:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጀግናውንና ተዋጊውን፤ ፈራጁንና ነቢዩን፤ አስማተኛውንና ሽማግሌውን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጀግናውንና ተዋጊውን፣ ፈራጁንና ነቢዩን፣ አስማተኛውንና ሽማግሌውን፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጀግኖቻቸውን፥ ወታደሮቻቸውን፥ ዳኞቻቸውንና ነቢያታቸውን፥ ሟርተኞቻቸውንና ሽማግሌዎቻቸውን፥ የጦር መኰንኖቻቸውንና አማካሪዎቻቸውን፥ ጠንቋዮቻቸውንና የወደፊቱን እናውቃለን የሚሉትን ሁሉ ነቃቅሎ ያጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያሉንም፥ ተዋጊውንም፥ ፈራጁንም፥ ነቢዩንም፥ ዐዋቂውንም፥ ሽማግሌውንም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያሉንም፥ ተዋጊውንም፥ ፈራጁንም፥ ነብዩንም፥ ምዋርተኛውንም፥ ሽማግሌውንም፥ |
ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች እያንዳንዱ በስዕሉ ቤት በጨለማ የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱም፦ “ጌታ አያየንም፥ ጌታ ምድሪቱን ትቶአታል፥ ብለዋልና።”