Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 3:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እነሆ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፉንና ርዳታውን፤ የምግብና የውሃ ርዳታውን ሁሉ ይነሣል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እነሆ፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፉንና ርዳታውን፣ የምግብና የውሃ ርዳታውን ሁሉ ይነሣል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እነሆ ጌታ የሠራዊት አምላክ፥ ሕዝቡ ኀይልና ብርታት አግኝተው የሚኖሩበትን ምግብና ውሃ፥ ሌላም ነገር ሁሉ ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ያስወግዳል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ከይ​ሁዳ ኀይ​ለ​ኛ​ውን ወን​ድና ኀይ​ለ​ኛ​ዋን ሴት፥ የእ​ን​ጃ​ራን ኀይል ሁሉ፥ የው​ኃ​ው​ንም ኀይል ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፍንና ብርታትን፥ የእንጀራን ድጋፍ ሁሉ የውሃውንም ድጋፍ ሁሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 3:1
19 Referencias Cruzadas  

የእንጀራችሁንም በትር በሰበርሁ ጊዜ፥ ዐሥር ሴቶች እንጀራችሁን በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፥ በሚዛንም መዝነው ዳግመኛ እንጀራችሁን ያመጡላችኋል፤ ትበላላችሁም ነገር ግን አትጠግቡም።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር ባለመታመን በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እጄን እዘረጋባታለሁ፥ የምግቧንም በትር እሰብራለሁ፥ ራብን እሰድድባታለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከእርሷ አጠፋለሁ፤


ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤ “በባላንጣዎቼ ላይ ቁጣዬን እገልጣለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ።


“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ኤርምያስን በጉድጓድ ውስጥ ጥለው ባደረጉበት ነገር ሁሉ ክፉ ነገርን ፈጽመዋል፤ በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለ ሌለ በዚያ በራብ ይሞታል።”


ንጉሡም ሴዴቅያስ አዘዘ፥ ኤርምያስንም በእስር ቤት አደባባይ አኖሩት፥ እንጀራም ሁሉ ከከተማይቱ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከጋጋሪዎች መንገድ ይሰጡት ነበር። እንዲሁም ኤርምያስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀምጦ ነበር።


ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።


ራፋስቂስ ግን፦ “አለቃዬ ይህን ቃል እንድናገር ወደ እናንተና ወደ አለቃችሁ ብቻ ልኮኛልን? እንደ እናንተ የራሳቸውን ኩስ ለመብላትና ሽንታቸውንም ለመጠጣት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎች ጭምር አይደለምን?” አላቸው።


ስለዚህ ሕዝቤ ዕውቀት በማጣቱ ይማረካል፤ መኳንንቱም በራብ ይሞታሉ፤ ሕዝቡም በውሃ ጥም ይቃጠላል።


እስትንፋስ አፍንጫው ላይ ባለች በሰው አትታመኑ፤ ከቶ ምን የሚበጅ ነገር አለው!


በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።


ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።


ምናሴ ኤፍሬምን፤ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


በእርግጥ ከጌታ ቁጣ የተነሣ ከፊቱ አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆነ፤ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


በአራተኛውም ወር በዘጠነኛው ቀን በከተማይቱ ራብ ጸንቶ ነበር፥ ለአገሬውም ሰው እንጀራ ታጣ።


ውኃችንን በብር ጠጣን እንጨታችንን በዋጋ ገዛን።


“እኔ በከተማችሁ ሁሉ ራብን፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣት አመጣባችኋለሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፥” ይላል ጌታ።


አሁንስ ለምን ጮክ ብልሽ ታለቅሻለሽ? በአንቺ ዘንድ ንጉሥ ስለ ሌለ ነውን? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የያዘሽ፥ መካሪሽ ስለ ጠፋ ነውን?


በዚያው ዓመት አራተኛው ወር በገባ በዘጠነኛው ቀን ራቡ በጣም ስለ ጸና ሕዝቡ የሚመገበው አንዳችም ምግብ አልነበረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios