ኢሳይያስ 19:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ግራ የመጋባት መንፈስ በውስጥዋ አፍሶባታል፤ ሰካራም በትፋቱ ዙሪያ እንደሚንገዳገድ እንዲሁ ግብጽን በሥራዋ ሁሉ እንድትንገዳገድ አደረጓት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የድንዛዜን መንፈስ አፍስሶባቸዋል፤ ሰካራም በትፋቱ ዙሪያ እንደሚንገዳገድ፣ ግብጽንም በምታደርገው ነገር ሁሉ እንድትንገዳገድ አደረጓት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተዘበራረቀ ምክር እንዲሰጡ ያደረጋቸውም እግዚአብሔር ነው፤ በመጨረሻም ግብጽ በሁሉ ነገር በመሳሳት የገዛ ትፋቱ አዳልጦት እንደሚጥለው ሰካራም ትንገዳገዳለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር የሚያስት መንፈስን ልኮባቸዋልና፤ ሰካርም፥ ደም ያዞረውም እንዲስት እንዲሁ ግብፃውያን በሥራቸው ሁሉ ሳቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የጠማምነትን መንፈስ በውስጥዋ ደባልቆአል፥ ሰካር በትፋቱ እንዲስት እንዲሁ ግብጽን በሥራዋ ሁሉ አሳቱ። |
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ አስደማሚ ነገርን ተአምራትንም እንደገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።
ስለዚህ ጌታ በጎበዛዝት ደስ አይሰኝም፤ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤ የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
አንተም፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምልከው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፥ ስከሩም፥ አስታውኩም፥ ውደቁም፥ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡም በላቸው።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ “የማያምንና ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት”