Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 48:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በጌታ ላይ ኰርቶአልና አስክሩት፤ ሞዓብም በጥፋቱ ላይ ይንከባለላል፥ ደግሞም መሳቂያ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “እግዚአብሔርን ንቋልና፣ ሞዓብን በመጠጥ አስክሩት። ሞዓብ በትፋቱ ላይ ይንከባለል፤ ለመዘባበቻም ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በእኔ ላይ ስለ ታበየች ሞአብን አጠጥታችሁ አስክሩአት፤ በትፋቷ ላይ ትንከባለል፤ ሕዝብም ይሳቅባት፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኰር​ቶ​አ​ልና፥ አስ​ክ​ሩት፤ ሞአ​ብም በት​ፋቱ ላይ ይን​ከ​ባ​ለ​ላል፤ በእ​ጁም ያጨ​በ​ጭ​ባል፤ ደግሞ መሳ​ቂያ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና አስክሩት፥ ሞዓብም በጥፋቱ ላይ ይንከባለላል፥ ደግሞም መሳቂያ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 48:26
37 Referencias Cruzadas  

ሞቅ ባላቸው ጊዜ ደስ እንዲላቸው ለዘለዓለምም አንቀላፍተው እንዳይነቁ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ አሰክራቸዋለሁም፥ ይላል ጌታ።


ሞዓብም በጌታ ላይ ኰርቶአልና ከእንግዲህ ወድያ ሕዝብ አይሆንም፥ እርሱም ይጠፋል።


ተደነቁ ደንግጡም፤ ጨፍኑ ታወሩም! ስክሩም፥ በወይን ጠጅ አይደለም፤ ተንገዳገዱ፥ በመጠጥ አይደለም።


ጌታ ግራ የመጋባት መንፈስ በውስጥዋ አፍሶባታል፤ ሰካራም በትፋቱ ዙሪያ እንደሚንገዳገድ እንዲሁ ግብጽን በሥራዋ ሁሉ እንድትንገዳገድ አደረጓት።


ሳን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፥ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።


ባቢሎን በጌታ እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፥ አሕዛብም ከወይን ጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ እንደ እብድ ሆነዋል።


እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ አለቀሱ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት ሰጠ! ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና መደንገጫ ሆኖአል።”


ፈርዖንም፦ “ቃሉን እንድሰማ እስራኤልንስ እንድለቅ ጌታ ማን ነው? ጌታን አላውቅም፥ እስራኤልንም ደግሞ አልለቅቅም” አለ።


ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንዲሰጣትም ታላቂቱ ባቢሎን በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።


እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።


በክብር ፈንታ እፍረት ሞልቶብሃል፤ አንተ ደግሞ ጠጣ፥ እንዳልተገረዘም ተቆጠር፤ የጌታ የቀኙ ጽዋ በአንተ ላይ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።


አንቺ ደግሞ ትሰክሪአለሽ፥ ትደበቂያለሽ፤ አንቺ ደግሞ ከጠላት የተነሣ መጠጊያን ትፈልጊአለሽ።


ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ።


ሳን። እኔ እየጮኽሁ እንደማለቅስ ሰምተዋል፥ የሚያጽናናኝ የለም፥ ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል፥ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፥ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቀን ታመጣለህ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።


አለቆችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ ገዢዎችዋንና ሹማምቶችዋን ኃያላኖችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም፥ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ የተባለው ንጉሥ።


በቁጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸውንም ምድር ላይ አፈሰስኩት።”


ከጌታ እጅ የቁጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ንቂ፥ ንቂ! ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል ጨልጠሽውማል።


መጥረቢያ በሚቆርጥበት ሰው ላይ ይኩራራልን? መጋዝስ በሚስበው ላይ ይታበያልን? በትር በሚያነሣው ሰው ላይ ራሱን እንደሚነቀንቅ፤ ዘንግም ዕንጨት እንዳልሆነ አድርጎ እንደሚኩራራ ነው።


እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህንን ያዋርዳል ያንንም ያከብራል።


አቤቱ፥ ጣልኸን አፈረስኸንም፥ ተቈጣኸን ጠግነን።


እነሆ፥ በአፋቸው ግሳት ይናገራሉ፥ ሰይፍም በከንፈሮቻቸው አለ፥ ማን ይሰማል? ይላሉ።


በሰማያት የሚቀመጠውም እርሱ ይሥቃል፥ ጌታም ይሣለቅባቸዋል።


ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ እርሱንስ ተዳፍሮ በደኅና የቆየ ማን ነው?


እንዳትለቅቃቸው አሁንም በሕዝቤ ላይ ትታበያለህ፤


ማዕዱ ሁሉ በትፋት ተሞልቶአል፤ ምንም ንጹሕ ስፍራ የለም።


እጁን በእግዚአብሔር ላይ ዘርግቶአልና፥ ሁሉን የሚችል አምላክን ደፍሮአልና፥


ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው፤ በዙሪያዋ ስፈሩባት አንድም ሰው አያምልጥ፤ በእስራኤል ቅዱስ በጌታ ላይ በኩራት አልታዘዝም ብላለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፥ እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios