ሙሴም፦ “ወጣቶቻችን፥ ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፥ በጎቻችንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ የጌታን በዓል እናደርጋለንና” አለ።
ሆሴዕ 5:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታንም ለመሻት በጎቻቸውንና በሬዎቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን ለመሻት፣ የበግና የፍየል መንጋ እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸውን ነድተው ሲሄዱ፣ እርሱ ስለ ተለያቸው፣ ሊያገኙት አይችሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ነድተው እግዚአብሔርን ለመፈለግ ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ስለ ተለያቸው አያገኙትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርንም ለመሻት ከበጎቻቸውና ከላሞቻቸው ጋር ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተለይቶአልና አያገኙትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርንም ለመሻት በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፥ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም። |
ሙሴም፦ “ወጣቶቻችን፥ ሽማግሌዎቻችን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን፥ በጎቻችንና ከብቶቻችን ከእኛ ጋር ይሄዳሉ የጌታን በዓል እናደርጋለንና” አለ።
ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከመራቁ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም።
በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቁርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው። እጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል፤
በጾሙ ጊዜ ልመናቸውን አልሰማም፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቁርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም፤ ይልቁንም በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ” አለኝ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ ከመቅደሴ ሊያርቁኝ፥ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚፈጽሙትን ታላቅ ርኩሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኩሰት ታያለህ።
የተመረጠውን መሥዋዕቴን ያቀርባሉ፥ ሥጋንም ያርዳሉ፥ ይበላሉም፤ ጌታ ግን በእነርሱ ደስ አይሰኝም፤ በደላቸውን አሁን ያስታውሳል፥ ስለ ኃጢአታቸውም ይቀጣቸዋል፤ እነርሱም ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።
“በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ መካከል በሮችን የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥” ይላል የሠራዊት ጌታ። ቁርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም።