Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ ከመቅደሴ ሊያርቁኝ፥ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚፈጽሙትን ታላቅ ርኩሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኩሰት ታያለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ደግሞም፣ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ከመቅደሴ ያርቀኝ ዘንድ በዚህ የሚያደርገውን እጅግ አስጸያፊ ነገር ታያለህን? ከዚህም የባሰ አስጸያፊ ነገር ታያለህ” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሆነውን ነገር ሁሉ ታያለህን? የእስራኤል ሕዝብ በዚህ ስፍራ የሚፈጽሙትን አጸያፊ ነገር ተመልከት፤ በዚህ አድራጎታቸው ከተቀደሰው ስፍራዬ እንድርቅ አድርገውኛል፤ ከዚህም የበለጠ እጅግ አስነዋሪ የሆነ ነገር ገና ታያለህ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ከመ​ቅ​ደሴ ያር​ቁኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በዚህ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን፥ ታላ​ቁን ርኵ​ሰት ታያ​ለ​ህን? ደግ​ሞም ተመ​ል​ሰህ ከዚህ የበ​ለጠ ታላቅ ርኵ​ሰት ታያ​ለህ” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ የሚያደርጉትን፥ ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉትን ታላቁን ርኵሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኵሰት ታያለህ አለኝ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 8:6
32 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር በእድፍሽ ሁሉና በርኩሰትሽም ሁሉ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ እኔም አሳንስሻለሁ፥ ዓይኔም አይራራም እኔም አላዝንም።


ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፥ እኔም እያየሁ ከምድር ተነሡ፥ ሲወጡም መንኰራኵሮች በአጠገባቸው ነበሩ፥ በጌታ ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ላይ ነበረ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ግባ፥ በዚህ የሚያደርጉትንም ክፉውን ርኩሰት ተመልከት።


ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፥ መንኰራኵሮችም በአጠገባቸው ነበሩ፥ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ።


ወደ ሰሜንም ወደሚመለከተው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር መግቢያ አመጣኝ እነሆ፥ ሴቶች ለታሙዝ እያለቀሱ በዚያ ተቀምጠው ነበር።


ሊያረክሱትም ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኩሰታቸውን አኖሩ።


ይህን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፥ ይህችንም ከተማ ለምድር አሕዛብ ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።’ ”


ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋልና፥ ሌላው ቀርቶ በቤቴ ውስጥ እንኳ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ፥ ይላል ጌታ።


“የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፥ ይላል ጌታ፤ ሊያረክሱትም ስሜ በተጠራበትን ቤት ውስጥ ርኩሰታቸውን አኑረዋል።


እነርሱስ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም አደባባይ ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?


ጌታም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፦ “ከዳተኛይቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ ከለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች በዚያም አመነዘረች።


በማኅበርና በጉባኤ መካከል ለክፉ ሁሉ ለመዳረግ ጥቂት ቀረኝ።”


የሴሎምን ማደሪያ ተዋት በሰዎች መካከል ያደረባትን ድንኳኑን፥


ጌታም አስታወቀኝ እኔም አወቅሁ፤ ሥራቸውንም ገለጥህልኝ።


ወደ አደባባዩ መግቢያም አመጣኝ፥ አየሁም፥ እነሆ በግንቡ ላይ ቀዳዳ ነበረ።


ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመለሱ፥ ከጣዖቶቻችሁም ተመለሱ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ፊታችሁን መልሱ።


ድሀውንና ችግረኛውን ቢያስጨንቅ፥ ቢቀማ፥ መያዣውን ባይመልስ፥ ዐይኖቹን ወደ ጣዖታት ቢያነሣ፥ ርኩሰትን ቢያደርግ፥


እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አይተሃልን? መራኝ፥ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ።


ጌታንም ለመሻት በጎቻቸውንና በሬዎቻቸውን ነድተው ይሄዳሉ፤ ነገር ግን እርሱ ከእነርሱ ተመልሶአልና አያገኙትም።


እንዲህም አላቸው፦ “ሌዋውያን ሆይ! ስሙኝ፤ ተቀደሱ፥ የአባቶቻችሁንም አምላክ የጌታን ቤት ቀድሱ፤ ርኩሱንም ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።


ደግሞም “ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኩሰት ሲያደርጉ ታያለህ” አለኝ።


የጌታ ክብር ከቤቱ መግቢያ ወጥቶ ከኪሩቤል በላይ ቆመ።


የጌታም ክብር ከከተማይቱ መካከል ተነሥቶ በከተማይቱ በምሥራቅ በኩል ባለው ተራራ ላይ ቆመ።


መድረካቸውን በመድረኬ አጠገብ፥ መቃናቸውን በመቃኔ አጠገብ በማድረጋቸው፥ በእኔና በእነርሱ መካከል ግንብ ብቻ ቀረ፥ በሠሩት ርኩሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ፥ ስለዚህ በቁጣዬ አጠፋኋቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios