ዘፍጥረት 18:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርስ አይፈርድምን? |
እንግዲህ አሁን ጌታን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በጌታ ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉንም ነገር ተጠንቅቃችሁ አድርጉ።”
ነገር ግን ኩላሊትንና ልብን የምትመረምር በቅንም የምትፈርድ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ሙግቴን ገልጬልሃለሁና በእነርሱ ላይ የሚሆነውን በቀልህን ልይ።
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?
እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ ቀና አይደለም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ ስሙ፥ በውኑ መንገዴ ቀና አይደለምን? ቀና ያልሆነውስ የእናንተ መንገድ አይደለምን?
እነርሱም በግምባራቸው ወድቀው በመስገድ እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ! አንተ የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ፥ አንድ ሰው ኃጢአት ቢሠራ አንተ በማኅበሩ ሁሉ ላይ ትቈጣለህን?”
በዚያን ጊዜ ፈራጆቻችሁን አዘዝኋቸው። አልኋቸውም፦ ‘የወንድሞቻችሁን ነገር ስሙ፥ በሰውና በወንድሙ ከእርሱም ጋር ባለው መጻተኛ መካከል በጽድቅ ፍረዱ።
በፍርድም አድልዎ አታድርጉ፥ ታላቁን እንደምትሰሙ፥ ታናሹንም እንዲሁ ስሙ፥ ፍርድ ለእግዚአብሔር ነውና ከሰው ፊት አትፍሩ፥ አንድ ነገር ቢከብዳችሁ እርሱን ወደ እኔ አምጡት፥ እኔም እሰማዋለሁ፤’
እኔ አልበደልሁህም፤ አንተ ግን በእኔ ላይ ዘምተህ በድለኸኛል፤ እንግዲህማ ፈራጅ የሆነው ጌታ በእስራኤላውያንና በአሞናውያን መካከል ዛሬ ይፍረድ።”