ገላትያ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጽሐፍም፥ እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፥ “አሕዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ፤” ብሎ አስቀድሞ ለአብርሃም ወንጌልን ሰበከለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጽሐፍ፣ እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ አስቀድሞ በማየት፣ “አሕዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ” በማለት ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ አስታወቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቅ ቅዱስ መጽሐፍ አስቀድሞ አይቶ “ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ” በማለት አስቀድሞ ለአብርሃም የምሥራቹን ቃል አብሥሮአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንደሚያጸድቃቸው መጽሐፍ አስቀድሞ ገልጦአልና፤ አሕዛብም ሁሉ በእርሱ እንዲባረኩ እግዚአብሔር አስቀድሞ ለአብርሃም ተስፋ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ። |
ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።
ከዐሥር አንድ ሰው እንኳን በምድሪቱ ቢቀር፤ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የባሉጥ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጉቶ እንደሚቀር፤ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጉቶ ሆኖ ይቀራል።”
የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር። ለብዙዎች እንደሆነ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደሆነ “ለዘርህም” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም እንዲህ የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ፦ “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የመሢሑ ሆነች፤ ለዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤”