Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 65:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከያዕቆብም ዘርን ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤ እኔም የመረጥኳቸው ይወርሷታል፥ አገልጋዬቼም በዚያ ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ከያዕቆብ ዘር የሆኑትን፣ ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሱትን አመጣለሁ። የተመረጠው ሕዝቤ ይወርሳቸዋል፤ ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ለያዕቆብ ልጆችን እሰጠዋለሁ፤ ይሁዳንም የተራሮቼን ርስት ወራሽ አደርገዋለሁ፤ እኔ የመረጥኩት ምድሪቱን ይይዛል፤ አገልጋዮቼም በዚያ ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የያ​ዕ​ቆ​ብን ዘርና የይ​ሁ​ዳን ዘር አመ​ጣ​ለሁ፤ የተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራ​ዬ​ንም ይወ​ር​ሳሉ፤ እኔ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸ​ውና ባሪ​ያ​ዎ​ችም ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በዚ​ያም ይኖ​ራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ከያዕቆብም ዘርን ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፥ እኔም የመረጥኋቸው ይወርሱአታል፥ ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 65:9
25 Referencias Cruzadas  

በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፥ እስራኤልም ያቈጠቁጣል፥ ያብባልም፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።


በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖር ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል።


ሕዝቤም በሰላም ማደሪያ፥ በታመነ ቤት፥ በጸጥተኛ ማረፊያ ይቀመጣል።


በስውር ወይም በጨለማ ምድር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ ጌታ እውነትን እናገራለሁ ትክክለኛውንም አወራለሁ።


የእስራኤልም ዘር ሁሉ በጌታ ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይከብራሉም።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፥ ምድርንም እንድታቀና፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች እንድታወርስ፥


ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል፤ ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፥ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።


ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እንድከብር የአታክልቴን ቡቃያ፥ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘለዓለም ይወርሳሉ።


ስማችሁንም ለተመረጡት ሕዝቤ እርግማን አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፥ ጌታ እግዚአብሔርም ይገድላችኋል፥ አገልጋዮቹንም በሌላ ስም ይጠራቸዋል።


ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።


ከመንግሥታት መካከል አወጣችኋለሁ፥ ከየአገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፥ ወደ ገዛ ምድራችሁም አመጣችኋለሁ።


በዚያ ዘመን እሰበስባችኋለሁ፥ በሰበሰብኳችሁም ጊዜ፤ ምርኮአችሁንም በዓይናችሁ ፊት በመለስሁ ጊዜ በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ለከበረ ስምና ለምስጋና አደርጋችኋለሁ፥ ይላል ጌታ።


እነዚያ ቀኖች ባያጥሩ ኖሮ ሥጋ የለበሰ ሁሉ ባልዳነ ነበር፤ ነገር ግን ስለ ተመረጡት ሰዎች እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ።


በወንጌልስ በኩል በእናንተ ምክንያት ጠላቶች ናቸው፤ በምርጫ በኩል ግን በአባቶች ምክንያት ተወዳጆች ናቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos