ሕዝቅኤል 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ጉልበቶችም ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅ ሁሉ ይዝላል፤ ጕልበት ሁሉ ውሃ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጆች ሁሉ ይዝላሉ፤ ጒልበቶች ሁሉ ይብረከረካሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅ ሁሉ ትደክማለች፤ ጕልበትም ሁሉ እንደ ውኃ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጅ ሁሉ ትደክማለች ጕልበትም ሁሉ እንደ ውኃ ትቀልጣለች። |
የሰው ልጅ ሆይ፥ ጩኽ ዋይም በል፥ በሕዝቤ ላይ ነውና፤ በእስራኤል አለቆች ሁሉ ላይ ነውና፤ እነርሱ ከሕዝቤ ጋር ወደ ሰይፍ ተጥለዋል፥ ስለዚህ ጭንህን ምታ።
እነርሱም ለምን ታለቅሳለህ? ሲሉህ እንዲህ በላቸው፦ ወሬ ስለሚመጣ ነው፥ ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስ ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበት ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳል፥ እነሆ ይመጣል ይፈጸማልም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።