ሕዝቅኤል 7:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ከእነርሱም የሚሸሹ ያመልጣሉ፥ እንደ ሸለቆ እርግቦች በተራራ ላይ ይሆናሉ፥ ሁሉም በኃጢአታቸው ላይ ያቃስታሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ተርፈው ያመለጡት ሁሉ በሸለቆ እንደሚኖሩ ርግቦች ስለ ኀጢአታቸው እያለቀሱ በተራራ ላይ ይሆናሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 የሸለቆ ርግቦች ራሳቸውን ለማዳን ወደ ተራራ እንደሚወጡ እንዲሁም ከሰዎቹ መካከል ከሞት የተረፉ ካሉ በተራራ ላይ ተገኝተው በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ሸለቆ ርግቦች የሐዘን እንጒርጒሮ ያሰማሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ከእነርሱም የሚሸሹ ይድናሉ፤ መብረርን እንደሚማር ርግብም በተራራ ላይ ይሆናሉ፤ እኔም በኀጢአታቸው ሁሉ እገድላለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ከእነርሱም የሚሸሹ ይድናሉ በተራራም ላይ ይሆናሉ፥ እኔም በኃጢአታቸው ሁሉን እገድላለሁ። Ver Capítulo |