Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 21:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የሰው ልጅ ሆይ፥ ጩኽ ዋይም በል፥ በሕዝቤ ላይ ነውና፤ በእስራኤል አለቆች ሁሉ ላይ ነውና፤ እነርሱ ከሕዝቤ ጋር ወደ ሰይፍ ተጥለዋል፥ ስለዚህ ጭንህን ምታ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የሰው ልጅ ሆይ፤ ይህ በሕዝቤ ላይ፣ በእስራኤልም መሳፍንት ሁሉ ላይ መጥቷልና፤ ጩኸት፣ ዋይታም አሰማ። እነርሱ ከሕዝቤ ጋራ በአንድ ላይ፣ ለሰይፍ ተጥለዋል፤ ስለዚህ ደረትህን ምታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የሰው ልጅ ሆይ! በሐዘን ጩኽ፤ ይህ ሰይፍ የተዘጋጀው ሕዝቤንና የእስራኤልን መሪዎች ለማጥፋት ነው። እነርሱም ከቀሩት ሕዝቤ ጋር ይገደላሉ፤ ስለዚህ በሐዘን ደረትህን ምታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የሰው ልጅ ሆይ! በሕ​ዝቤ ላይ ነውና፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አለ​ቆች ሁሉ ላይ ነውና ጩኽ፤ ዋይም በል፤ እነ​ርሱ ከሕ​ዝቤ ጋር ለሰ​ይፍ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል፤ ስለ​ዚህ እጅ​ህን ጽፋ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የሰው ልጅ ሆይ፥ በሕዝቤ ላይ ነውና፥ በእስራኤል አለቆች ሁሉ ላይ ነውና ጩኽ ዋይም በል፥ እነርሱ ከሕዝቤ ጋር ለሰይፍ ተሰጥተዋል፥ ስለዚህ ጭንህን ጽፋ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 21:12
17 Referencias Cruzadas  

አንተም የሰው ልጅ ሆይ አልቅስ፥ ወገብህን በማጉበጥና በምሬት በፊታቸው አልቅስ።


የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።


በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፥ ዋይ ዋይ እላለሁ፥ ባዶ እግሬንና ራቁቴን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፥ እንደ ሰጎን ልጆችም የዋይታ ድምፅ አሰማለሁ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አልቅሱ፥ ለቀኑ ወዮ!


አንተም የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር፥ መዳፍህን በመዳፍህ ምታ፥ የተገደሉ ሰዎች ሰይፍ ሦስት ጊዜ ይደጋግም የሚከብባቸው የተገደለ የታላቅ ሰው ሰይፍ ነው።


እነርሱ ሲገድሉ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ሳለሁ በግምባሬ ተደፍቼ ጮኽሁ፥ እንዲህም አልሁ፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! መዓትህን በኢየሩሳሌም ላይ ስታፈስስ የእስራኤልን ትሩፍ ሁሉ ታጠፋለህን?


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእጅህ አጨብጭብ፥ በእግርህም እየረገጥህ፥ ስለ የእስራኤል ቤት ክፉ የርኩሰት ሥራዎቻቸው ሁሉ ወዮ! በል፤ በሰይፍ፥ በራብና በቸነፈር ይወድቃሉና፤


ከተመለስሁ በኋላ ተጸጸትሁ፥ ከተገሠጽሁም በኋላ በኀዘን ጭኔን ጸፋሁ፤ የብላቴንነቴንም ስድብ ተሸክሜአለሁና አፈርሁ ተዋረድሁም።’


ይመጣሉ በጽዮንም ተራራ ላይ ሆነው እልል ይላሉ፤ ስለ ጌታም በጎነቱ፥ ስለ እህሉና ስለ ወይን ጠጁ፥ ስለ ዘይቱም፥ ስለ በጎቹና ስለ ከብቶቹ በሐሤት ይሞላሉ፤ ነፍሳቸውም ውኃ ጠጥታ እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፥ ከእንግዲህም ወዲህ አያዝኑም።


“ልትታረዱና ልትበተኑ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ።


ሰይፉ እንዲወለወል፥ በእጅም እንዲያዝ ተሰጠ፤ በገዳዩ እጅ እንዲቀመጥ ተሳለ፥ ተወለወለም።


ፈተና ተደርጓል፥ ደግሞ የተናቀ በትር ባይኖርስ ምን ይሆናል? ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


አንተም ቀንህ የደረሰብህ፥ የኃጢአትህ ቀጠሮ ጊዜ የደረሰብህ፥ ርኩስ ኃጢአተኛ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥


እነሆ የእስራኤል ልዑሎች እያንዳንዱ እንደ አቅሙ ደም ሊያፈስሱ በአንቺ ውስጥ ነበሩ።


ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል።


እጆች ሁሉ ይዝላሉ፥ ጉልበቶችም ሁሉ እንደ ውኃ ይፈስሳሉ።


የጌታ ቀን መጥቷልና፥ እርሱም ቀርቧልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios