ሕዝቅኤል 45:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል መሪዎች ሆይ፥ ይብቃችሁ፤ ግፍንና ጭቆናን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፤ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አንሱ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የእስራኤል ገዦች ሆይ! ከልክ ዐልፋችኋል፤ ይብቃችሁ፤ ዐመፅንና ጭቈናን ተዉ፤ ቀናና ትክክል የሆነውን ነገር አድርጉ። የሕዝቤን ርስት መቀማት ይቅርባችሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የእስራኤል መሪዎች! እነሆ ለረጅም ጊዜ ኃጢአት ስትሠሩ ኖራችኋል፤ አሁን ግን ግፍንና ጭቈናን አቁሙ! ቅንና ትክክል የሆነውን ነገር ሥሩ! ሕዝቤ እንደገና ከምድራቸው ተፈናቅለው እንዲባረሩ አታድርጉ! ይህን የምነግራችሁ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእስራኤል አለቆች ሆይ! ይብቃችሁ፤ ግፍንና ዐመፅን አስወግዱ፤ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፤ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል አለቆች ሆይ፥ ይብቃችሁ፥ ግፍንና ብዝበዛን አስወግዱ፥ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፥ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። |
ጌታ እንዲህ ይላል፦ ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ የተበዘበዘውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ፤ መጻተኛውንና ድሀ አደጉን መበለቲቱንም አትበድሉ፥ አታምፁባቸውም፥ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
በጉድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋትዋ ከእርሷ ውስጥ ይፈልቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእርሷ መካከል ይሰማል፥ ደዌና ቁስልም ሁልጊዜ በፊቴ አለ።
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ ይህን አይተሃልን? በዚህ የሰሩትን ርኩሰት ሊያደርጉ ለይሁዳ ቤት ይህ ቀላል ነገር ነውን? ምድሪቱን በዓመፅ ሞልተዋታል፥ ሊያስቆጡኝም ተመልሰዋል፥ እነሆ ቅርንጫፉን ወደ አፍንጫቸው አቅርበዋል።
ወታደሮችም እንዲሁ፦ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ “ማንንም በግፍ ወይም በሐሰት ክስ አትበዝብዙ፤ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ፤” አላቸው።
አሕዛብ እንደሚያደርጉት በመዳራት፥ በሥጋዊ ምኞት፥ በስካር፥ በመሶልሶል፥ ያለ ልክ በመጠጣት፥ በአስነዋሪ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።