La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 30:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በግብጽ ላይ ሰይፍ ይመጣል፥ የተገደሉት በግብጽ ውስጥ ሲወድቁ፥ በኢትዮጵያ ጭንቀት ይሆናል፤ ብዛትዋን ይወስዳሉ፥ መሠረቶቿንም ያፈርሳሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በግብጽ ላይ ሰይፍ ይሆናል፤ በኢትዮጵያም ላይ ጭንቀት ይመጣል። የታረዱት በግብጽ ሲወድቁ፣ ሀብቷ ይወሰዳል፤ መሠረቶቿም ይፈርሳሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በግብጽ ጦርነት ይሆናል፤ በኢትዮጵያም አስጨናቂ ሁከት ይደርሳል፤ ብዙዎች በግብጽ ምድር ይገደላሉ፤ አገሪቱም ተመዝብራ መሠረቶችዋ ይናጋሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰይፍ በግ​ብፅ ላይ ይመ​ጣል፤ ሁከ​ትም በኢ​ት​ዮ​ጵያ ይሆ​ናል፤ የተ​ገ​ደ​ሉ​ትም በግ​ብፅ ውስጥ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳሉ፤ መሠ​ረ​ቷም ይፈ​ር​ሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፥ የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ ይወድቃሉ፥ ብዛትዋንም ይወስዳሉ፥ መሠረትዋም ይፈርሳል።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 30:4
19 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማ፤ ሁሉም ዋይታ ያሰማሉ፤ ስለ ቂርሐራሴት መሠራት በጥልቅ ኀዘን ታለቅሳላችሁ።


በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት፥


ግብፃውያንን በግብፃውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድም ወንድሙን፥ ባልንጀራም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።


ጌታም እንዲህ አለ፦ “አገልጋዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት እንዲሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥


ፈረሶች ሆይ! ውጡ፤ ሰረገሎችም ሆይ! ንጐዱ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፉጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።


የጌታ በቀል ነውና በዙሪያዋ ሆናችሁ በእርሷ ላይ ጩኹ፤ እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ ቅጥሮችዋም ፈረሱ፤ እርሷን ተበቀሉ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።


ቸነፈርንም በእርሷ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


የግብጽን ምድር ባድማ በሆኑ አገሮች መካከል ባድማ አደርጋታለሁ፥ ከተሞችዋንም በፈረሱት ከተሞች መካከል ለአርባ ዓመት ባድማ ይሆናሉ፤ ግብጻውያንንም ወደ ሕዝቦች እበትናቸዋለሁ፥ በአገሮችም እዘራቸዋለሁ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የግብጽን ምድር ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እሰጠዋለሁ፤ ብዛትዋን ያነሳል፥ ምርኮዋን ይማርካል፥ ብዝበዛዋንም ይበዘብዛል፤ ይህም ለሠራዊቱ ደመወዝ ይሆናል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሰይፍ አመጣብሻለሁ፥ ሰውንና እንስሳንም ከአንቺ አጠፋለሁ።


ሁሉም ጋሻና የራስ ቁር የለበሱ ፋርስ፥ ኢትዮጵያና ፉጥም ከእነርሱ ጋር።


እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።