ሕዝቅኤል 28:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 ቸነፈርንም በእርሷ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 በርሷ ላይ መቅሠፍት አመጣለሁ፤ በመንገዶቿ ላይ ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ ከየአቅጣጫው በሚመጣ ሰይፍ፣ የታረዱት በውስጧ ይወድቃሉ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 መቅሠፍቴን በእናንተ ላይ አመጣለሁ፤ በየመንገዱም ደም እንዲፈስስ አደርጋለሁ፤ በየአቅጣጫው በሚነሣባችሁ ጦርነት ምክንያት በመካከላችሁ ሰዎች ይገደላሉ፤ ሕዝቦችም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ቸነፈርንም በአንቺ ላይ፥ ደምንም በጎዳናሽ ላይ እሰድዳለሁ፤ ከዙሪያሽም በላይሽ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልሽ ይወድቃሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ቸነፈርንም በእርስዋ ላይ፥ ደምንም በጎዳናዋ እሰድዳለሁ፥ ከዙሪያዋ በላይዋ ባለ ሰይፍ የተወጉ በመካከልዋ ይወድቃሉ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። Ver Capítulo |