ሕዝቅኤል 3:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምላስህን ከትናጋህ ጋር አጣብቃታለሁ፥ አንተም ዲዳ ትሆናለህ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና የሚገስጽ ሰው አትሆንባቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐመፀኛ ቤት ቢሆኑም ልትገሥጻቸው እንዳትችል ምላስህን ከላንቃህ ጋራ አጣብቃለሁ፤ ድዳም ትሆናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ዐመፀኛ ሕዝብ ማስጠንቀቅ እንዳትችል አንደበትህ እንዲተሳሰር አደርገዋለሁ፤” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ምላስህን ከትናጋህ ጋር አጣብቃታለሁ፤ አንተም ዲዳ ትሆናለህ፤ እነርሱም ዐመፀኛ ቤት ናቸውና የሚዘልፍ ሰው አትሆንባቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ምላስህን ከትናጋህ ጋር አጣብቃታለሁ አንተም ዲዳ ትሆናለህ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና የሚዘልፍ ሰው አትሆንባቸውም። |
ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፥ መወርወሪያዎችዋን አጠፋ፤ ሰበረም፤ ንጉሥዋና አለቆችዋ ሕግ በሌለባቸው በአሕዛብ መካከል አሉ፥ ነቢዮችዋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላገኙም።
የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፥ እንዲያዩ ዐይን አላቸው ነገር ግን አያዩም፥ እንዲሰሙም ጆሮ አላቸው ነገር ግን አይሰሙም፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።
አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የስደተኛ ጓዝ ለራስህ አዘጋጅ፥ እያዩህም በቀን ወደ ምርኮ ሂድ፥ በፊታቸውም እንደ ምርኮኛ ከስፍራህ ወደ ሌላ ስፍራ ሂድ፥ ዓመፀኛ ቤት ቢሆኑም ምናልባት ያስተውሉ ይሆናል።
በዚያን ቀን አፍህ ላመለጠው ሰው ይከፈታል፥ ትናገራለህም፥ ከዚያ በኋላም ድዳ አትሆንም። ስለዚህ ምልክት ትሆናቸዋለህ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።