Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 3:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ነገር ግን በተናገርሁህ ጊዜ አፍህን እከፍታለሁ፥ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ የሚሰማ ይስማ፥ የማይሰማም አይስማ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ነገር ግን በምናገርህ ጊዜ አፍህን እከፍታለሁ፤ አንተም፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ ትላቸዋለህ። የሚሰማ ይስማ፤ የማይሰማም አይስማ፤ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ዳግመኛ ስናገርህና አንደበትህን ስከፍትልህ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ “ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እነርሱ ዐመፀኞች ስለ ሆኑ ለመስማት የሚፈቅዱ ይስሙ፥ ለመስማት የማይፈቅዱ ይተዉት።’ ”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ነገር ግን በተ​ና​ገ​ር​ሁህ ጊዜ አፍ​ህን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ሰማ ይስማ፤ እንቢ የሚ​ልም እንቢ ይበል” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ነገር ግን በተናገርሁህ ጊዜ አፍህን እከፍታለሁ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና አንተ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሚሰማ ይስማ፥ የማይሰማም አይስማ ትላቸዋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 3:27
17 Referencias Cruzadas  

ጌታ ያሳየኝን ነገር ሁሉ ለምርኮኞቹ ተናገርሁ።


ፊታቸው የተኮሳተረና ልባቸውም የደነደነ ልጆች ናቸው፥ እኔ ወደ እነርሱ እልክሃለሁ፥ አንተም እንዲህ በላቸው፦ “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤”


እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ በመካከላቸው ነቢይ እንደ ነበረ ያውቃሉ።


በዚያን ቀን አፍህ ላመለጠው ሰው ይከፈታል፥ ትናገራለህም፥ ከዚያ በኋላም ድዳ አትሆንም። ስለዚህ ምልክት ትሆናቸዋለህ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


በዚያ ቀን ለእስራኤል ቤት ቀንድን አበቅላለሁ፥ ለአንተ ደግሞ በመካከላቸው የተከፈተ አፍን እሰጥሃለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ተነሥተህም ወደ ተማረኩት፥ ወደ ሕዝብህ ልጆች ሂድ፥ እነርሱም ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው።


ምላስህን ከትናጋህ ጋር አጣብቃታለሁ፥ አንተም ዲዳ ትሆናለህ፥ እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና የሚገስጽ ሰው አትሆንባቸውም።


ግምባርህን ከባልጩት እንደሚጠነክር አልማዝ አድርጌዋለሁ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና አትፍራቸው፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ።


ያመለጠው ሰው ከመምጣቱ በፊት በነበረው ምሽት የጌታ እጅ በእኔ ላይ ነበረች፥ በነጋውም ወደ እኔ እስኪመጣ ድረስ አፌን ከፈተ፤ አፌም ተከፈተ ከዚያም በኋላ ዲዳ አልሆንሁም።


እነሆ አንተ እንደ ጥሩ ዘፈን፥ እንደ መልካም ድምፅ፥ እንደ ጎበዝ ተጫዋች ሆነህላቸዋል፤ ቃልህንም ይሰማሉ ነገር ግን አያደርጉትም።


የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።


የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”


ተቃዋሚዎቻችሁ በሙሉ ሊቃወሙትና ሊከራከሩት የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና።


ቃል እንዲሰጠኝና አፌን በመክፈት የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንዳስታውቅ፥ ስለ እኔም ለምኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos