La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 27:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፋርስ፥ ሉድና ፉጥ በሠራዊትሽ ውስጥ ወታደሮችሽ ነበሩ፤ ጋሻና ራስ ቁርም በአንቺ ውስጥ ሰቀሉ፤ ውበትን ሰጡሽ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘የፋርስ፣ የሉድና የፉጥ ሰዎች፣ ወታደር ሆነው በሰራዊትሽ ውስጥ አገለገሉ፤ ሞገስም ይሆኑሽ ዘንድ፣ ጋሻቸውንና የራስ ቍራቸውን በግድግዳሽ ላይ ሰቀሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ከፋርስ፥ ከልድያና ከሊቢያ የመጡ ወታደሮች በሠራዊትሽ ውስጥ ያገለግላሉ፤ ጋሻቸውንና የራስ ቊራቸውን በጦር ሰፈርሽ ሰቅለዋል፤ እነርሱ ለአንቺ ክብር ያስገኙ ሰዎች ናቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፋር​ስና ሉድ፥ ሊብ​ያም በሠ​ራ​ዊ​ትሽ ውስጥ ሰል​ፈ​ኞ​ችሽ ነበሩ፤ ጋሻና ራስ ቍርም በአ​ንቺ ውስጥ ያን​ጠ​ለ​ጥሉ ነበር፤ እነ​ር​ሱም ክብ​ር​ሽን ሰጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፋርስና ሉድ ፉጥም በሠራዊትሽ ሰልፈኞችሽ ነበሩ፥ ጋሻና ራስ ቍርም በአንቺ ውስጥ ያንጠለጥሉ ነበር፥ እነርሱም ውበትሽን ሰጡ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 27:10
15 Referencias Cruzadas  

የምጽራይም ዘሮች ሉድ፥ ዐናማውያን፥ ለሃባውያን፥ ናፍሐውያን፥


የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ እና አራም ናቸው።


የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ እና ከነዓን ናቸው።


ምጽራይምም የወለደው ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍተሂምን፥


የሴምም ልጆች፤ ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌቴር፥ ሞሳሕ ናቸው።


የካምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው።


አንገትሽ ለጦር ዕቃ መስቀያ እንደ ተሠራው እንደ ዳዊት ግንብ ነው፥ ሺህ ጋሻ የኃያላንም መሣሪያ ሁሉ ተንጠልጥሎበታል።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።


ፈረሶች ሆይ! ውጡ፤ ሰረገሎችም ሆይ! ንጐዱ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፉጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።


በአንቺ ላይ ሙሾ ያወርዳሉ፥ እንዲህም ይሉሻል፦ ከባሕር የተቀመጥሽ በባሕርም ውስጥ የጸናሽ፥ ከሚቀመጡብሽም ጋር በዙሪያሽ የሚኖሩትን ሁሉ ያስፈራሽ፥ ዝነኛ ከተማ ሆይ፥ እንዴት ጠፋሽ!


የአርቫድ ልጆችና ሠራዊቶችሽ በቅጥሮችሽ ላይ ዙሪያውን ነበሩ፥ ጋማዳውያንም በግንቦችሽ ውስጥ ነበሩ፤ ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፥ ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።


ኢትዮጵያ፥ ፉጥ፥ ሉድ፥ ባዕዳን ሁሉ፥ ኩብና የቃል ኪዳኑ ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።


ሁሉም ጋሻና የራስ ቁር የለበሱ ፋርስ፥ ኢትዮጵያና ፉጥም ከእነርሱ ጋር።


ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኃይልዋ ነበሩ፤ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ።