Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 1:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የሴምም ልጆች፤ ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌቴር፥ ሞሳሕ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የሴም ልጆች፤ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው። የአራም ልጆች፤ ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሜሼኽ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሑል፥ ጌቴርና ሜሼክ ሲሆኑ፥ እነርሱም በስሞቻቸው ለሚጠሩ ሕዝቦች የነገድ አባቶች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የሴ​ምም ልጆች፤ አይ​ላም፥ አሡር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ የአ​ራ​ምም ልጆች፤ ኡስ፥ ዑል፥ ጋቴር፥ ሞሳክ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የሴምም ልጆች፤ ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሳሕ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 1:17
22 Referencias Cruzadas  

ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፥ እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነው።


የሴም ትውልድ ይህ ነው። ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ሴም መቶ ዓመት በሆነው ጊዜ፥ አርፋክስድ የተባለ ልጅ ወለደ።


በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፥ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፥ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፥ በአሕዛብ ንጉሥ በቲድዓል ዘመን እንዲህ ሆነ


አራዴዎንን፥ ሰማሪዎንን፥ አማቲንን ነበር።


አርፋክስድም ሼላሕን ወለደ፤ ሼላሕም ዔቦርን ወለደ።


ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶች አለቆች ቀርበው፦ “እንደ እናንተ አምላካችሁን እንፈልገዋለን፥ የአሦር ንጉሥ ኤሳርሐዶን ወደዚህ ካመጣን ቀን ጀምሮ ለእርሱ እንሠዋ ነበርና፥ ከእናንተ ጋር እንሥራ” አሉአቸው።


ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፥


በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።


አስጨናቂ ራእይ ተነገረኝ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፥ ውጪ! ሜዶን ሆይ፥ ክበቢ፤ ጭንቀቷን ሁሉ አጠፋለሁ።


ኤላምም ከሰረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፥ ቂርም ጋሻውን አነገበ።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።


የዘምሪ ነገሥታትንም ሁሉ፥ የኤላም ነገሥታትንም ሁሉ፥ የሜዶን ነገሥታትንም ሁሉ፥


ፋርስ፥ ሉድና ፉጥ በሠራዊትሽ ውስጥ ወታደሮችሽ ነበሩ፤ ጋሻና ራስ ቁርም በአንቺ ውስጥ ሰቀሉ፤ ውበትን ሰጡሽ።


ሐራን፥ ካኔ፥ ዔድን፥ የሳባ ነጋዴዎች፥ አሦርና ኪልማድ ነጋዴዎችሽ ነበሩ።


አሦርና ጉባኤዋ ሁሉ በዚያ አሉ፤ በሰይፍ ወድቀው በተገደሉባት ሰዎች ሁሉ መቃብር ተከባለች።


ኤላምም በዚያ አለች ብዛትዋም ሁሉ በመቃብሯ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያሸበሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር ወርደዋል፥ ወደ ጉድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል።


ከእናንተ ጋር ቃላትን ውሰዱ፥ ወደ ጌታም ተመለሱ፥ እንዲህም በሉት፦ “በደልን ሁሉ አስወግድ፥ በቸርነትም ተቀበለን፥ በእንቦሳም ፋንታ የከንፈራችንን ፍሬ እንሰጣለን።


በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ‘ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን አውግዝልኝ አለኝ።’


የቃይናን ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos