ሕዝቅኤል 21:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንገት ላይ ያኖሩህ ዘንድ ከንቱን ራእይ ነገር ሲያዩልህ በሐሰትም ምዋርት ሲናገሩልህ፦ ሰይፍ፥ ሰይፍ ተመዝዞአል፥ ይገድልም ዘንድ ያብረቀርቅም ዘንድ ተሰንግሎአል በል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታለመልህ የሐሰት ራእይ፣ የተነገረልህ የውሸት ሟርት ቢኖርም፣ የግፍ ጽዋቸው በሞላ፣ ቀናቸው በደረሰ፣ መታረድ በሚገባቸው ክፉዎች፣ ዐንገት ላይ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምታዩት ራእይ ሐሰት ነው፤ የምትናገሩትም የትንቢት ቃል ውሸት ነው፤ እናንተ ክፋትና ርኲሰት የሞላችሁ ናችሁ፤ ለመጨረሻ ጊዜ ቅጣት የምትቀበሉበት ቀን ቀርቦአል፤ በአንገታችሁ ላይ ሰይፍ ተቃጥቶአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተገደሉት ኀጢአተኞች አንገት ላይ ያኖሩህ ዘንድ ከንቱ ራእይን ሲያዩልህ፥ በሐሰት ምዋርትም ሲናገሩልህ፥ በኀጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ ቀናቸው ደረሰ። |
በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፥ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ።
እናንተ ግን፦ ለባቢሎን ንጉሥ አታገለግሉም የሚሉአችሁን ነብዮቻችሁንና ምዋርተኞቻችሁን፥ ሕልም አላሚዎቻችሁንና ቃላተኞቻችሁን መተተኞቻችሁንም አትስሙ፤
በጉድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋትዋ ከእርሷ ውስጥ ይፈልቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእርሷ መካከል ይሰማል፥ ደዌና ቁስልም ሁልጊዜ በፊቴ አለ።
ኖን። ነቢዮችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፥ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፥ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል።
ስለዚህ ከዚህ በኋላ ከንቱ ራእይን አታዩም፥ ምዋርትም አታሟርቱም፥ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።