Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 21:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አንተም ቀንህ የደረሰብህ፥ የኃጢአትህ ቀጠሮ ጊዜ የደረሰብህ፥ ርኩስ ኃጢአተኛ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ ‘አንተ የግፍ ጽዋህ የሞላ፣ የምትቀጣበት ቀን የደረሰ፣ ርኩስና ክፉ የእስራኤል መስፍን ሆይ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “አንተ ክፋትና ርኲሰት የሞላብህ የእስራኤል መሪ! ለመጨረሻ ጊዜ የምትቀጣበት ቀን እነሆ ቀርቦአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አን​ተም ቀን​ህና የኀ​ጢ​አ​ትህ ቀጠሮ ጊዜ የደ​ረ​ሰ​ብህ፥ ርኩስ ኀጢ​አ​ተኛ የእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ሆይ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አንተም ቀንህ የደረሰብህ፥ የኃጢአትህ ቀጠሮ ጊዜ የደረሰብህ፥ ርኩስ ኃጢአተኛ የእስራኤል አለቃ ሆይ፥

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 21:25
21 Referencias Cruzadas  

ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።


ጌታ ግን ይሥቅበታል፥ ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።


ጽዮንን ክበቡአት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ ግንቦችዋንም ቁጠሩ፥


ጌታ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፥ አቤቱ፥ እንደጽድቄ ፍረድልኝ፥ እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።


“ነገር ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከክፋቱ የተነሣ ሊበላ እንደማይችል እንደ ክፉው በለስ፥ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አለቆቹንም፥ በዚህችም አገር የሚቀሩትን የኢየሩሳሌምን ትሩፍ፥ በግብጽም አገር የሚቀመጡትን ክፉውን አደርግባቸዋለሁ።


ስለ አሞን ልጆች፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን? ታዲያ ሚልኮምስ ጋድን ለምን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቹ ላይ ለምን ተቀመጠ?


ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ቀኖች ይመጣሉ፥ ይላል ጌታ፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፥ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፥ እስራኤልም የወረሱትን ይወርሳል፥ ይላል ጌታ።


አንቺ በብዙ ውኃ አጠገብ የተቀመጥሽ፥ በመዝገቦችም የበለጠግሽ ሆይ! የእንጀራሽ ገመድ ተበጥሶዋል ፍጻሜሽ ደርሶአል።


ኢዮአቄምም እንዳደረገው ሁሉ በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር አደረገ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና የናቀውን መሐላዬን ያፈረሰውንም ቃል ኪዳኔን በራሱ ላይ አመጣለሁ።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ጩኽ ዋይም በል፥ በሕዝቤ ላይ ነውና፤ በእስራኤል አለቆች ሁሉ ላይ ነውና፤ እነርሱ ከሕዝቤ ጋር ወደ ሰይፍ ተጥለዋል፥ ስለዚህ ጭንህን ምታ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ኃጢአታችሁን ስለ አሰባችሁ መተላለፋችሁም ስለ ተገለጠ ኃጢአታችሁም በሥራችሁ ሁሉ ስለ ታየ እናንተም ስለ ታሰባችሁ፥ በእጅ ትያዛላችሁ።


አንገት ላይ ያኖሩህ ዘንድ ከንቱን ራእይ ነገር ሲያዩልህ በሐሰትም ምዋርት ሲናገሩልህ፦ ሰይፍ፥ ሰይፍ ተመዝዞአል፥ ይገድልም ዘንድ ያብረቀርቅም ዘንድ ተሰንግሎአል በል።


ራባን የግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ፤ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።


ቀኑ ቅርብ ነውና፥ የጌታ ቀን ቅርብ ነው፥ የደመና ቀን፥ የሕዝቦች ጊዜ ይሆናል።


የዘለዓለም ጥል ስላለህ በመጨረሻው የፍርዳቸው ጊዜ፥ በመከራቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፥


የሰው ልጅ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ፍጻሜ! በአራቱም የምድሪቱ ማዕዘናት ላይ ፍጻሜ መጥቷል።


አሁን ፍጻሜ በአንቺ ላይ ነው፥ ቁጣዬን በአንቺ ላይ እሰድዳለሁ፥ እንደ መንገድሽም እፈርድብሻለሁ፥ ርኩሰትሽንም ሁሉ እመልስብሻለሁ።


ፍጻሜ መጥቷል፥ ፍጻሜ መጥቷል፥ በአንቺ ላይ ነቅቷል፥ እነሆ፥ መጥቷል።


በረባት ቅጥር ላይ እሳትን አነዳለሁ፤ በጦርነትም ቀን በጩኸት፥ በዐውሎ ነፋስም ቀን በሁከት የእርሷን የንጉሥ ቅጥሮች ትበላለች፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos