ሕዝቅኤል 22:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)28 ነቢዮችዋ ጌታ ሳይናገር “ጌታ እንዲህ ይላል” እያሉ የሐሰት ራእይ በማየትና በውሸት ሟርት፥ በኖራ ይለቀልቋቸዋል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም28 ነቢያቷም በሐሰት ራእይና በውሸት ሟርት ይህን ሁሉ ድርጊት ያድበሰብሱላቸዋል፤ እግዚአብሔርም ሳይናገር፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል’ ይላሉ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም28 ነቢያቱ ግድግዳን ኖራ እንደሚቀባ ሰው ይህን ሁሉ ኃጢአት ይሸፍናሉ፤ በሐሰት ራእይ አየን ይላሉ፤ የውሸት ትንቢትም ይናገራሉ፤ ይህ የልዑል እግዚአብሔር ቃል ነው ይላሉ፤ ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር ምንም ቃል አልነገርኳቸውም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)28 ነቢያቶቻቸውም ይቀቡአቸዋል፤ ከንቱ ነገርንም ያዩላቸዋል፤ እግዚአብሔር እንዲህ አለ እያሉም በሐሰት ያምዋርቱላቸዋል፤ እግዚአብሔር ግን አልነገራቸውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)28 እግዚአብሔርም ሳይናገር ነቢያቶችዋ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል። Ver Capítulo |